Popular Posts

Monday, April 2, 2018

የድካም ክብር

የኢየሱስ የመጨረሻው ሃይሉ የተገለጠው በድካሙ እንጂ በሃይሉ አልነበረም፡፡ የኢየሱስ ሃየል የተገለጠው በሞቱ ነበር፡፡   
በድካም ተሰቅሎአልና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል በሕይወት ይኖራል። 2 ቆሮንቶስ 13፡4
አለም አይቶ የማያውቀውን ታላቁን የትንሳኤ ሃይል ያየነው በኢየሱስ ድካም ነው፡፡ ኢየሱስ በሞቱ ነው ህይወትን ያሳየን፡፡
ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤ ኤፌሶን 1፡20-21
ኢየሱስ በሞት ላይ ስልጣን ያለውን ዲያቢሎስን የሻረው በህይወት አይደለም በድካምና በሞቱ ነው ፡፡
እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ እብራዊያን 2፡14-15
እኛም በራሳችን ስንደክም ያን ጊዜ የእግዚአብሄር ሃይል ያድርብናል፡፡ የሰው ሃይል ሲያልቅ የአግዚአብሄር ሃይል ይጀምራል፡፡
እኛ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንደክማለንና፥ ነገር ግን ስለ እናንተ በሆነ በእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋር በሕይወት እንኖራለን። 2ኛ ቆሮንቶስ 13፡4
በራሳችን ስንደክም በእግዚአብሄር ሃይለኛ ነንና፡፡ በመከራ ስናልፍ በራሳችን ስንደክም የእግዚአብሄር ሃይል በእኛ በሃይል ይሰራል፡፡  
እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና። 2ኛ ቆሮንጦስ 12፡9-10
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#ኢየሱስ #እግዚአብሄር #ድካም #ሞት #ህይወት #ትንሳኤ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #መመካት #ብርታት #እምነት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment