Popular Posts

Thursday, April 5, 2018

እግዚአብሄርን የሚያከብር ምስጋና

ምስጋና የሚሠዋ ያከብረኛል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን ለእርሱ የማሳይበት መንገድ ከዚያ አለ። መዝሙር 5023
እግዚአብሄርን ማመስገን የመንፈሳዊ ጤንነት ምልክት ነው፡፡
የዋህነት የመንፈሳዊ ጤንነት ምልክት ነው፡፡
ብልጣብልጥ ሰው እግዚአብሄርን ሊያመሰግን አይችልም፡፡ ብልጣብልጥ ሰው ነገሮች የሚሆኑለት በብልጠቱ ይመስለዋል፡፡ በአራድነት መኖር የሚፈልግ ሰው የራሱን ቅልጥፍና እንጂ እግዚአብሄርን ሊያመሰግን አይችልም፡፡  
እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፤ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል። ዕንባቆም 2፡4
ትህትና የመንፈሳዊ ጤንነት ምልክት ነው፡፡
ትእቢተኛ የሆነ ሰው ከእግዚአብሄር በላይ ሁሉን የሚያውቅ የሚመስለው ሰው እግዚአብሄርን አያመሰግንም፡፡ ትሁት ሰው የማላውቅው ነገር አለ እግዚአብሄር ሁሉን ያውቃል ለሚል ሰው እግዚአብሄርን ለማመስገን ይቀለዋል፡፡
ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?  ሚክያስ 6፡8
እምነት የመንፈሳዊ ጤንነት ምልክት ነው፡፡
በማየት የማይመላለስ ሰው ነገሩ ከመሆኑ በፊት እግዚአብሄርን ያመሰግናል፡፡ በዝቅታ ውስጥ እግዚአብሄርን ለማመስገን ከፍታን ማየት ይጠይቃል፡፡ በተቀራኒ ሁኔታዎች ውስጥ እግዚአብሄርን ለማመስገን የሚታየውን አለማየት የማይታየውን ማየት ይጠይቃል፡፡ 
የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡17-18
እግዚአብሄርን ሃይልና ጥበብ ማወቅ የመንፈሳዊ ጤንነት ምልክት ነው፡፡
እግዚአብሄርን የሚያውቅ ሰው በእግዚአብሄር ላይ አያጉረመርምም፡፡ እግዚአብሔርን የሚያውቅ ሰው እግዚአብሄርን ሁል ጊዜ ያመሰግነዋል፡፡  
ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ፦ መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ኢሳይያስ 40፡27-28
የእግዚአብሄርን መልካምነት ማወቅ የመንፈሳዊ ጤንነት ምልክት ነው፡፡
እግዚአብሄርን የሚያውቅ ሰው እግዚአብሄር መልካም እንደሆነ እንጂ ሌላ እውቀት ስለሌለው ነበገር ሁሉ እግዚአብሄርን ያመሰግናል፡፡  
እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ሮሜ 8፡28
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ማካፈል share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #አመስግኑ #መልካም #እምነት #ቃልኪዳን #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #እወጃ #የዘላለምህይወት #ቸር #መንፈስ #መንፈስቅዱስ

No comments:

Post a Comment