አባቶቻችን
በዚህ ተራራ ሰገዱ፤ እናንተም፦ ሰው ሊሰግድበት የሚገባው ስፍራ በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ አለችው። ኢየሱስም እንዲህ አላት፦ አንቺ ሴት፥ እመኚኝ፥ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣል። እናንተስ ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ፤ እኛ መዳን ከአይሁድ ነውና ለምናውቀው እንሰግዳለን። ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፥ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ያስፈልጋቸዋል። ዮሐንስ 4፡20-24
ኢየሱስ
ከሳምራዊትዋ ሴት ጋር ሲነጋገር ለሁላችን ትልቅ መረዳትን የሚሰጥን ነገር ተናግሮዋል፡፡ ሳምራዊትዋ ሴት ሳምራዊያን በዚያ ተራራ
ላይ ለእግዚአብሄር እንደሚሰገድ እንደሚያምኑ አይሁዳዊያን ደግሞ የሚሰገደው በኢየሪሳሌም ነው እንደሚሉና ተናገረች፡፡
ኢየሱ
የመለሰላት መልስ ግን ከሁለቱም ለየት ያለ ነበር፡፡ ኢየሱስ በአዲሱ ኪዳን ሰው በዚያ ተራራም ይሁን በኢየሩሳሌም እግዚአብሄር እንደማይሰገድለት
አስተማራል፡፡
እግዚአብሄር
መንፈስ ነው፡፡ እግዚአብሄር በተራራ ላይ አይኖርም፡፡ እግዚአብሄር በኢየሩሳሌም አይኖርም፡፡
እግዚአብሄር በሁሉም ቦታ ይገኛል፡፡
ነገር ግን ነቢዩ፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት
ቤት ትሠራላችሁ? ይላል ጌታ፥ ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድር ነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው አይደለምን? እንዳለ፥ ልዑል የሰው
እጅ በሠራችው አይኖርም። ሃዋሪያት 7፡48-50
እግዚአብሄር ሰው በሰራው ቤተመቅደስ ውስጥ አይኖርም፡፡ እግዚአብሄርን በሆነ ቤት ውስጥ ብንፈልገው አናገኘውም፡፡
ፈሪሳውያንም፦ የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች ብለው ቢጠይቁት፥ መልሶ፦ የእግዚአብሔር
መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም፤ ደግሞም፦ እንኋት በዚህ ወይም፦ እንኋት በዚያ አይሉአትም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ
ናትና አላቸው። ሉቃስ 17፡20
ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና
እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም፤ ሃዋሪያት 17፡24
እግዚአብሄር መንፈስ ነው፡፡ እግዚአብሄር በስጋ አይገኝም፡፡ እግዚአብሄ በአንድ
አገር ውስጥ አይገኝም፡፡ እግዚአብሄር በአንድ ከተማ ውስጥ አይገኝም፡፡ እግዚአብሄር በአንድ ቤት ውስጥ አይገኝም፡፡ እግዚአብሄር
በአንድ ስፍራ አይገኝም፡፡
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ
ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? ኢሳያስ 66፡1
ለእግዚአብሄር የሚሰግዱለት ሰዎች በመንፈስ ሊያገኙት ይገባል፡፡ እግዚአብሄርን የሚያገኙት
ሰዎች በመንፈስ ብቻ ሊያገኙት ይችላሉ፡፡ ለእግዚአብሄር የሚሰግዱለት ሰዎች በመንፈስ ብቻ ሊሰግዱለት ይችላሉ፡፡
እግዚአብሄር የሚፈልገው በስጋ የሚሰግዱለትን ሰዎች አይደለም፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው
በመንፈስ የሚሰግዱለትን ሰዎች ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው በእውነትና በመንፈስ የሚሰግዱለትን ሰዎች ነው፡፡ ለእግዚአብሄር በልባቸው
የሚሰግዱለትን ሰዎች ይፈልጋል፡፡
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰማይ ዙፋኔ ነው፥ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ
ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው? እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፤
ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፥ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፥ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ። ኢሳያስ 66፡2
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #እግዚአብሄር #አምልኮ #ስግደት #እውነት #መንፈስ #ኢየሩሳሌም #ቅዱሳን
#ጌታ #ሰማእታት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #እምነት #ክብር #ፍቅር #ምስል #ሰላም #ደስታ #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #ኦርቶዶክስ #ማርያም #አንድ #ብቻ #ሰይጣን
No comments:
Post a Comment