Popular Posts

Friday, April 27, 2018

እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ

በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። 1ኛ ዜና 16፡10-11
መፅሃፍ ቅዱስ እግዚአብሄርን ስለመፈለግ ግልፅ ነው፡፡
ለምሳሌ መፅሃፍ ቅዱስ ብዙ ብር ያለው ሰው ደስ ይበልው አይልም፡፡ እንዲያውም ባለጠጋ በእግዚአብሄር እንጂ በብልጥግናው እንዳይመካ ነው መፅሃፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ ሃያል በሃይሉ ደስ ይበለው አይልም፡፡ እንዲያውም ሃያል ምሕረትንና ፍርድን ጽድቅንም በምድር ላይ የሚደርግ እግዚአብሔር መሆኑን በማወቁና በማስተዋሉ እንጂ በሃይሉ እንዳይመካ መፅሃፍ ቅዱስ ያስጠነቅቃል፡፡
መፅሃፍ ቅዱስ ጠቢብ በጥበቡ ደስ ይበለው አይልም፡፡ እንዲያውም ጠቢብ አለምን ከሰማይ በፍቅር እና በጥበብ በሚያስተዳደር በእግዚአብሄር እንጂ በጥበቡ አይመካ ነው የሚለው፡፡
እግዚአብሄር በምንም እንዳንመካ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር በእርሱ እንጂ በሌላ በምንም ነገር እንዳንመካ ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄር ግን በግልፅ ደስ ሰው እንዲሰኝ የሰጠው ነገር እግዚአብሄርን መፈለግ ብቻ ነው፡፡
ጤነኛ ልብ እግዚአብሄርን ይፈልጋል፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈልግ ልብ እየበረታ ይሄዳል፡፡   
እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ። እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ። ኤርምያስ 29፡12-13
እግዚአብሄርን የሚፈልግ ሰው እግዚአብሄርን ያገኘዋልና ደስ ይበለው፡፡ ሰው በህይወቱ የሚያስፈልገው እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈልግ ሰው በህይወቱ የሚያስፈልገውን ብቸኛ ነገር ስለሚያገኝ ደስ ለመሰኘት በቂ ምክኒያት ነው፡፡ እረኛውን እግዚአብሄርን ያገኘ ሰው ሁሉ ሁሉንም ነገር አገኘ፡፡
እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። መዝሙር 23፡1
እግዚአብሄር ሃያል አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈልግ ሰው ሃያሉን እግዚአብሄርን ያገኛል፡፡ እግዚአብሄርን የሚፈልግን ሰው እግዚአብሄር ያፀናዋል፡፡ እግዚአብሄርን በሚፈልገው ሰው ቦታ የራሱን ብርታት ያሳያል፡፡
ሁልጊዜ በእግዚአብሄር እርዳታ መኖር የሚፈልግ አንዳንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ መፈለግ አለበት፡፡ በህይወቱ ሳያቋርጥ ክንዱን እንዲገልፅ የሚፈልግ ሰው እግዚአብሄርን መፈለግ ማቋረጥ የለበትም፡፡
በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው። እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። 1ኛ ዜና 16፡10-11
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ፀሎት #ሁሉንቻይ #ጥበኛ #ሁሉበሁሉ #እግዚአብሔር #እግዚአብሔርንመፈለግ #ፀሎት #የዘላለምህይወት #የእግዚአብሔርፈቃድ #የጊዜው #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ብፅእና  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment