ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። ዘዳግም 33:26
የፈጠረን እግዚአብሄር ነው፡፡ የሚረዳን እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄር በሰማይ ያለው ሊረዳን ነው፡፡ እግዚአብሄር እኛን ከመርዳት ውጭ ሌላ ስራ የለውም፡፡ የእግዚአብሄር ስራ እኛን መርዳት ነው፡፡
እግዚአብሄር በሰማይ ያለው እኛን ለመርዳት ብቻ ሳይሆን እግዚአብሄር በሰማይ ያለው በታላቅነት ነው፡፡ እግዚአብሄር በታላቅነት በሰማይ ያለው ሊረዳን ነው፡፡
እግዚአብሄር ከፍ ያለ ቦታ ያለው ሁሉን ሊያይና ሊረዳን ነው፡፡
የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ። መዝሙር 53፡2
ስለዚህ ነው የእግዚአብሄርን እርዳታ ያየው መዝሙረኛው ዳዊት እግዚአብሄርን እንዲህ እያለ የሚያመሰግነው፡፡
ረዳቴ ሆነኸኛልና፥ በክንፎችህም ጥላ ደስ ይለኛልና። መዝሙር 63፡7
እግዚአብሄር አምላኩ የሆነለት ህዝብ ምስጉን ነው፡፡
የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ ተስፋውም በአምላኩ በእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምስጉን ነው፤ መዝሙር 146፡5
ህዝቡን እንደሚረዳና እንደሚደግፍ እንደ እግዚአብሄር ያለ ማንም የለም፡፡ እንደ እኛ የታደለ ሰው የለም፡፡ እንደ እኛ ደስ ሊለው የሚገባው ሰው የለም፡፡ እንደ እኛ ሳያቋርጥ እግዚአብሄርን ማመስገን የሚገባው ሰው የለም፡፡ እግዚአብሄር በሰማይ ያለው እኛን ሊረዳ ነው፡፡
ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም። ዘዳግም 33:26
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#እምነት #እርዳታ #ታላቅነት #ቃል #መልካም #መታመን #መደገፍ #መንፈስቅዱስ #ቃሉንመስማት #ረድኤት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment