በየአመቱ ኤፕሪል 1 ቀን የማሞኛ ቀን ተብሎ በብዙ ሰዎች ዘንድ ሰውን ዋሽቶ ማታለል እንደመዝናኛ ይቆጠራል፡፡ አንዳንድ ሰው ሰውብ ማስደንገጥ ደስ የሚለው ሰው አለ፡፡ እኔ በበኩሌ ሰውን ማስደንገጥ በፍፁም አልወድም፡፡
ትንታግንና ፍላጻን ሞትንም እንደሚወረውር እንደ ዕብድ ሰው፥ ባልንጀራውን የሚያታልል፦ በጨዋታ አደረግሁት የሚል ሰውም እንዲሁ ነው። ምሳሌ 26፡18-19
ሰው ሰውን ሊያታልለው ይችላል፡፡ አንዳንድ ሰው ግን ራሱን ያታልላል፡፡ በጣም በአስፈላጊ እና ወሳኝ ነገር ላይ ራሱን የሚያታልል ሰው እንዳለ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡
ሰነፍ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐስቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም። መዝሙር 14፡1
The fool says in his heart, “There is no God.” They are corrupt, their deeds are vile; there is no one who does. Psalm 14:1
የሚገርመው ነገር ሰነፍ በልቡ ነው እግዚአብሄር የለም የሚለው፡፡ እግዚአብሄር የለም ማለቱ የሚታወቀው በድርጊቱ ብቻ ነው፡፡ የሚኖረው ኑሮ ሁሉ እግዚአብሄር እንደሌለ ነው የሚያሳየው፡፡ እግዚአብሄር የለም ብሎ ያስባል፡፡ እግዚአብሄር እንደሌለ እንደማይፈርድ አድርጎ ያስባል፡፡ እግዚአብሄር እንደሌለ እንደማይሰራ አድርጎ ይናገራል፡፡ እግዚአብሄር እንደሌለ የፈለገውን ማድረግ እንደሚችል አድርጎ ይመላለሳል፡፡
ሰነፍ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል። ረከሱ በበደላቸውም ጐሰቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚያደርጋት የለም። መዝሙር 53፡1
እግዚአብሄር የለም የሚል ሰው ተጠያቂነትን አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር የለም የሚል ሰው ራሱን መግዛት አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር የለም የሚል ሰው ለማንም ተጠሪ መሆን አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር የለም የሚል ሰው እንደልቡ መኖር ነው የሚፈልገው፡፡
ሰው እግዚአብሄር አለ ካለ እግዚአብሄርን በየእለቱ መፈለግ አለበት፡፡ ሰው እግዚአብሄር አለ ካለ የእግዚአብሄርን ፈቃድ መፈለግና መከተል አለበት፡፡ ሰው እግዚአብሄር አለ ብሎ ካመነ እግዚአብሄርን በነገር ሁሉ መፍራት አለበት፡፡ ሰው እግዚአብሄር አለ ካለ ለእግዚአብሄር ተጠያቂነት አለበት፡፡
ሰነፍ ወይም ሞኝ ለስንፍናው ማሳበቢያ የሚያገኘው እግዚአብሄር የለም በማለት ነው፡፡ እግዚአብሄር የለም በማለቱ እግዚአብሄርን ከመፈለግ ፣ ፈቃዱን ከማድረግና ለእግዚአብሄር ካለ የህይወት ሃላፊነቶች ሁሉ የዳነ ይመስለዋል፡፡ በዚህም ራሱን ያታልላል፡፡
ሰው ጥበበኝነቱና ትጋቱ የሚታወቀው ለእግዚአብሄር መኖር እውቅና በመስጠቱ ብቻ ነው፡፡
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ። ምሳሌ 1፡7
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ጥበብ #ቤተክርስትያን #ሞኝ #ሰነፍ #በልቡ #እግዚአብሔር #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ማስተዋል #እምነት #ፈተና #ፀሎት #ጌታ #የእግዚአብሄርቃል #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment