Popular Posts

Wednesday, December 13, 2017

ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች

መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና። ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ። ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፦ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ። ሉቃስ 2፡10-14
ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን
ኢየሱስ የተወለደው ለህዝብ ሁሉ ነው፡፡ ኢየሰስ የተወለደው ለፍጥረት ሁሉ ነው፡፡ ኢየሱስ የመጣው ከሴት ለተወለደ ሰው ሁሉ ነው፡፡
ታላቅ ደስታ የምሥራች
የኢየሱስ መወለድ የምስራች ነው፡፡ የኢየሱስ መወለድ መልካም ዜና ነው፡፡
መልካሙን የምሥራች የሚያወሩ እግሮቻቸው እንዴት ያማሩ ናቸው ተብሎ እንደ ተጻፈ ካልተላኩ እንዴት ይሰብካሉ? ሮሜ 10፡15
አትፍሩ
የኢየሱስ መወለድ የሰውና የእግዚአብሄር መታረቅ የመጀመሪያው ደረጃ ነው፡፡ የኢየሱስ መወለድ የኢየሱስ መወለድ ድስ ይምንሰኝበት ዘና የምንልበት እንጂ የምንፈራበት አይደለም፡፡ ፍርሃት ነግሶ ከነበረ ፍርሃት ከዚህ በኋላ አይኖርም፡፡  
በእርሱም ከጠላቶቻችን እጅ ድነን በዘመናችን ሁሉ ያለ ፍርሃት በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ እንድናገለግለው ሰጠን። ሉቃስ 1፡74-75
ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና
የተቀባ አዳኝ ጌታ የሆነ ኢየሱስ ተወልዶልናል፡፡
ክብር ለእግዚአብሔር
ሰው በእግዚአብሄር ክብር ተፈጥሯል፡፡ ሰዊች ኢየሱስን በመቀበል የእግዚአብሄ ልጆች ይሆናለሁ ወደ ልጅነት ክብራቸው ይመለሳሉ፡፡ ሰዎች ኢየሱስን ሲቀበሉ እግዚአብሄርን ማከበር ይችላሉ፡፡ ለእግዚአብሄር የሚገባውን ክብር መስጠት የሚችለው ሰው ኢየሱስን በመጀመሪያ በመቀበሉ ነው፡፡
ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ። 1ኛ ጴጥሮስ 1፡23
ሰላምም በምድር
ሰው እውነተኛ ሰላምን የሚለማመደው በኢየሱስ ነው፡፡ በኢየሱስ ያለውን ሰላም ያላየ ሰው እውነተኛውን ሰላም ገና አላየም፡፡ ኢየሱስ የሚሰጠውቅ ሰላም አለም እንደሚሰጠው አይደለም፡፡
ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም። ዮሃነስ 14፡27
ለሰውም በጎ ፈቃድ
እግዚአብሄር ለሰዎች ያለውን በጎ ፈቃድ ያሳየው በኢየሱስ ነው፡፡ ሰው ሁሉ እረኛ እንደሌለው በግ ተቅበዝብዞ ጠፍቶ በነበረበት ጊዜ እግዚአብሄር ኢየሱስን ላከልን፡፡ የእግዚአብሄር በጎ ፈቃድ የተገለጠው በኢየሱስ መወለድ ነው፡፡ እግዚአብሄር ለሰዎች ያለውን ርህራሄና ልብ ያየነው በኢየሱስ መወለድ ነው፡፡
ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል። ሮሜ 5፡8
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #መወለድ #ገና #ክሪስማስ #ማማጥ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ጥሪ #አላማ #መፅሃፍቅዱስ #ሰላም #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ #አትፍሩ #የምስራች #ደስታ #ክብር #ሰላም #በጎፈቃድ

No comments:

Post a Comment