ሕፃን
ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ . . . የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። ኢሳይያስ 9፡6
የአለቅነት
ብቸኛው ጥቅም ሰዎች ሲገለገሉና ሲጠቀሙ ማየት ነው፡፡ አለቅነት በራሱ ጥቅም አይደለም፡፡ የአለቅነት ጥቅም ሰዎች ካሉበት እግዚአብሄር
ወደ አየላቸው ደረጃ ሲደርሱ ማየት ነው፡፡ አለቅነት ሰዎች ከታሰሩበት ነገር ተፈትተው በነፃነት እግዚአብሄርን ሲያገለግሉ ማየት
ነው፡፡
አለቅነትን
ለራሳቸው ጥቅም የሚጠቀሙበት ሰዎች በአለም ላይ ስላሉ አለቅነት ከጥቅም ጋር ተያይዞዋል፡፡ በአገራችንም ያለውም አባባል ሲሺም ያልበላ
ሲሻር ይቆጨዋል የሚለው አባባል የመጣው አለቅነትን ከተጠቃሙነት ጋር አያይዞ ነው፡፡ ነግር ግን አባባሉ መሆን የነበረበት "ሲሾም
በትጋትና በታማኝነት ህዝብን ያላገለገለ ሲሻር ይቆጨዋል" መሆን ነበረበት፡፡ አለቅነት ሰውን ከመጥቀም ያለፈ ጥቅም የለውም፡፡
አለቅነት ግን እግዚአብሄርን አገልግሎ ከእግዚአብሄር ሽልማትን ከመቀበል ውጭ ጥቅማ ጥቅም የለውም፡፡
የአለቅነትን
ሃላፊነት የተረዱ ሰዎች አለቅነትን እንደ ጥቅም አይጓጉለትም፡፡ የአለቅነት ሃላፊነትን የተረዱ ሰዎች ሸክሙ እንጂ ጥቅሙ ትዝ አይላቸውም፡፡
የአለቅነትን ሸክም የተረዱ ሰዎች አላቅነትን እንደጥቅም አይፈልጉትም፡፡
እርግጥ
ነው በአለም ያሉ ሰዎች አለቅነትን እንደመጠቀሚያ ይጠቀሙበታል፡፡ በአለም ያሉ ሰዎች ከሰው ውስጥ ትልቁን ድርሻ ለመጠቀም የአለቅነትን
ስልጣን በጭካኔ ይጠቀሙበታል፡፡ በአለም ብዙ አለቅነት ያለው ብዙ ይጠቀማል ትንሽ አለቅነት ያለው ትንሽ ይጠቀማል፡፡ በአለም ያሉ
ሰዎች አለቅነትን ሰውን ለመበዝበዝ ይጠቀሙበታል፡፡
ኢየሱስ
ግን ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ የአሕዛብ አለቆች እንዲገዙአቸው ታላላቆቹም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ። ማቴዎስ
20፡25-26
አለቅነትን
ለራስ ጥቅም መጠቀሚያ ማድረግ የእግዚአብሄር ሃሳብ አይደለም፡፡ አለቅነት የመጠቀሚያ መንገድ አይደለም፡፡
በእናንተ
ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን
ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤ 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5፡2-3
አለቅነት
ሃላፊነት ነው፡፡ አለቅነት ሸክም ነው፡፡ አለቅነት የትጋት ስራ ነው፡፡ አለቅነት ታማኝነት ነው፡፡ አለቅነት መሰጠት ነው፡፡ አለቅነት
ፊት ቀዳሚነት ነው፡፡ አለቅነት ማንም ባያደርገው እኔ አደርገዋለሁ ማለት ሃላፊነት መውሰድ ነው፡፡ አለቅነት ምሪትን በየጊዜው በመስጠት
የመጥቀም የማገልገል መንገድ ነው፡፡
በእናንተስ
እንዲህ አይደለም፤ ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፥ ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ
የእናንተ ባሪያ ይሁን፤ እንዲሁም የሰው ልጅ ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም። ማቴዎስ
20፡26-28
አለቅነት ሰላምን መስጠት ነው፡፡ አለቅነት ሰዎችን
ወደ ሰላም ምንም ወዳልጎደለበትና ምንም ወዳልተበላሸበት ቦታ መርቶ ማድረስ ነው፡፡
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ሰላም #ድንቅመካር #ሃያልአምላክ
#የሰላምአለቃ #የዘላለምአባት
#ኢየሱስ #ክርስቶስ
#ጌታ #ማገልገል
#ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት
#እምነት #መፅሃፍቅዱስ
#መንፈስቅዱስ #አለቅነት
#ፌስቡክ #አቢይዋቁማ
#አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment