በእኔ
ኑሩ፤ እኔም በእናንተ፤ ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ከአልኖረ ብቻውን ሊያፈራ እንደማይችል እናንተም እንዲሁ በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም። በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ዮሐንስ 15፡4፣7
ፍሬያማነት በኢየሱስ መኖር እንደሆነ የፍሬያማነትብቸኛው መንገድ በሚለው በፅሁፌ አስረድቻለሁ፡፡
በኢየሱስ መኖር ማለት በቃሉ መኖር ማለት ነው፡፡
ኢየሱስን መስማት ማለት ቃሉን መስማት ማለት ነው፡፡ ኢየሱስን መታዘዝ ማለት ቃሉን መታዘዝ ማለት ነው፡፡ ኢየሱስን መከተል ማለት
ቃሉን መከተል ማለት ነው፡፡
ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው
ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ ማቴዎስ 28፡19
እውነተኛ ፍሬያማነት የሚመጣው በኢየሱስ በመኖር
ነው፡፡ በኢየሱስ መኖርን ደግሞ ከባድ አላደረገውም፡፡ በኢየሱስ ላለመኖር ምንም ሰበብ እስከማይኖረን ድረስ ቀላል አድርጎታል፡፡
በኢየሱስ መኖር ማለት ደግሞ በቀላሉ በቃሉ መኖር ማለት ነው፡፡ በቃሉ ካልኖርን በኢየሱስ አልኖርንም፡፡ በቃሉ ከኖርን በኢየሱስ
ኖረናል በዚያም ደግሞ ፍሬ እናፈራለን፡፡
በእኔ ኑሩ፤ እኔም በእናንተ፤ ቅርንጫፍ በወይኑ
ግንድ ከአልኖረ ብቻውን ሊያፈራ እንደማይችል እናንተም እንዲሁ በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም። በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ
ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል። ዮሐንስ 15፡4፣7
ለተጨማሪ ፅሁፎች
https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች
https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#ኢየሱስ #ጌታ #ሬያማነት
#ፍሬ #ማፍራት
#ስኬት #በእኔኑሩ
#ቃል #ቤተክርስትያን
#አማርኛ #ስብከት
#መዳን #መፅሃፍቅዱስ
#ሰላም #አቢይ
#አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
#መመዘኛ #መስፈርት
#ፅናት #ትግስት
#መሪ
No comments:
Post a Comment