ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ፦ መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፤ በሙሉ በሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ኃጢአት በሚሰዋ መሥዋዕት ደስ አላለህም። በዚያን ጊዜ፦ እነሆ፥ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ አልሁ ይላል። ዕብራውያን 10፡5-7
እግዚአብሄር ሰውን ለክብሩ ፈጥሮታል፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው እርሱን እየታዘዘ ምድርን እንዲገዛ ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰውን የፈጠረው ለራሱ አላማ ነው፡፡ ሰው በወደደው መንገድ እግዚአብሄርን እንዲያገለግል እግዚአብሄር ሰውን አልፈጠረውም፡፡ ሰው በወደደው መንገድ እንዲያገለግለው እግዚአብሄር ሰውን አልፈጠረውም፡፡
እግዚአብሄር ስውን የፈጠረው ሰው እግዚአብሄርን እየታዘዘ በምድር ላይ የእግዚአብሄርን ፈቃዱን እንዲፈፅም ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሄር የጠየቀውን ነገር ከማድረግ ከመታዘዝ ይልቅ ይልቅ በራሳችን የፈጠራ ሃሳብ እግዚአብሄርን ልናስደስተው መፈልግ ከንቱ ድካም ነው፡፡ እግዚአብሄር አድርግ ያለውን ሳይሆን በራሳችን አነሳሽነት ለእግዚአብሄር የተለያዩ መባዎችና መስዋእቶች በማቅረብ እግዚአብሄርን የምናስደስተው ከመሰለን ተሳስተናል፡፡ እግዚአብሄ ታዛዥ ልጅነ እንጂ የፈጠራን ሰው አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር አዳዲስ የማስደሰቻ መንገድ እንዲፈጥረለት ሰውን አይጠብቅም፡፡ እግዚአብሄር ምን መሆን እንዳለበት እግዚአብሄር ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር ከሰው የሚፈልገው አንድ ነገር መታዘዝን ብቻ ነው፡፡
ሰው በራሱ ሃሳብ እንዲያስደስተው እግዚአብሄር አይጠብቅምም አይፈልግምም፡፡ ሰው ካልታዘዘው ምንም ታላላቅ መስዋእቶች ቢያደርግለትም እግዚአብሄር በሰው አይደሰትም፡፡
ሰው እግዚአብሄር አድርግልኝ ያለውን ትቶ የተለያየ መስዋእትን ቢያቀርብ እግዚአብሄርን ደስ አያሰኘውም፡፡
ስለዚህ ነው ኢየሱስ ከድንግል ማርያም ሲወለድ እንዲህ ተብሎ የተፃፈው፡፡
ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ፦ መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፤ በሙሉ በሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ኃጢአት በሚሰዋ መሥዋዕት ደስ አላለህም። ዕብራዊያን 10፡5-6
ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው እግዚአብሄር ያልጠየቀውን ሌላ ተጨማሪ መስዋእትንት ሊያደርግ ሳይሆን እግዚአብሄርን ሊታዘዝ ነው፡፡ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው በራሳ አነሳሽነት አንድ ተጨማሪ መባ ሊሰጥ ሳይሆን የእግዚአብሄርን አላማ ሊፈፅም ነው፡፡
በዚያን ጊዜ፦ እነሆ፥ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ አልሁ ይላል። ዕብራውያን 10፡7
በራስ አነሳሽነት መስዋእትን በማድረግ እግዚአብሄርን ማስደሰት ባዶ ሃይማኖተኝነት ነው፡፡ እግዚአብሄርን የሚያስደስተው አንድ ነገር እግዚአብሄር የሚፈልገውን ፈቃዱን አግኝቶ ማድረግ ነገር ነው፡፡
አሁንም እግዚአብሄር ከእኛ በራስ አነሳሽነት የሚደረግ መስዋእትና መባን አይፈልግም፡፡ እግዚአብሄር የሚፈልገው ያዘዘንን እንደድናደርግ ነው፡፡ ያዘዘንን ካደረግን እግዚአብሄርን እናስደስተዋለን፡፡ መባንና መስዋእትን እያደረግን ያዘዘንን ካላደረግን ግን እግዚአብሄርን በፍፁም አናስደስተውም፡፡ መባንና መስዋእትን ባናደርግ እንኳን እግዚአብሄርን በየእለቱ ከታተዘን በቂ ነው፡፡ እግዚአብሄርን በመባና በመስዋት የምናስደስተው ብቸኛ መንገድ እርሱ ከጠየቀን ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር በመባችንና በመስዋእታችን ደስ የሚሰኝበት ብቸኛ መንገድ እርሱን ታዝዘነው ስናደርገው ብቻ ነው፡፡
እግዚአብሄር የእስራኤልን ህዝብ እርሱ ለመስዋእት ምንም እንደማይጓጓ እነርሱ በመስዋት የሚያቀርቡለት ነገር ሁሉ የእርሱ የራሱ እንደሆነ ያስታውሳቸዋል፡፡ ከዚያ ይልቅ የጠየቀውን እንዲያደርጉለት እንዲታዘዙት ያዛቸዋል፡፡
ሕዝቤ፥ ስማኝ፥ ልንገርህ፤ እስራኤልም፥ ስማኝ፥ ልመስክርብህ፤ አምላክስ እኔ አምላክህ ነኝ። ስለ ቍርባንህ የምዘልፍህ አይደለሁም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህ ሁልጊዜ በፊቴ ነው። ከቤትህ ፍሪዳን ከመንጋህም አውራ ፍየልን አልወስድም፤ የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ በሺህ ተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእኔ ናቸውና። የሰማይን አዕዋፍ ሁሉ አውቃለሁ፥ የምድረ በዳ አራዊትም በእኔ ዘንድ ናቸው። ብራብም ለአንተ አልነግርህም፥ ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና። የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን? የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን? ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፤ መዝሙር 50፡7-14
ለእግዚአብሄር አምልኮ ነገራችንን መስጠት ሳይሆን ራሳችንን መስጠት ነው፡፡ ራሱን ያልሰጠ ሰው ምንም ነገር እግዚአብሄርን አያስደስተውም፡፡ እግዚአብሄር ከእኛ የሚፈልገው ፈቃዳችንን ለእርሱ ፈቃድ እንድናስገዛ እንጂ ነገራችንን ብቻ እንድንሰጠው አይደለም፡፡ እግዚአብሄር በመስዋእት እንዲቀርብን የሚፈልገው የሰው ፈቃድ እንጂ መስዋእት አይደለም፡፡ እግዚአብሄር ማየት የሚፈልገው የሰውን ፈቃድ መሸነፍ እንጂ የመባና የመስዋእትን መአት አይደለም፡፡
እግዚአብሄ ኢየሱስ በምድር ላይ እንዲወለድ የሰውን ስጋ ያዘጋጀለት እንዲታዘዘው ነው፡፡ እግዚአብሄር በራሳቸው አነሳሽነት ሳይታዘዙት መስዋእት የሚያደርገለትን አልፈለገም፡፡ ፈቃዱን የሚያስገዛ የሚታዘዘን ሰው ስለፈለገ ነው እግዚአብሄር ለኢየሱስ ስጋን ያዘጋጀውና ከሰው እንዲወለድ ያደረገው፡፡
ስለዚህ ወደ ዓለም ሲገባ፦ መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ፤ በሙሉ በሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ኃጢአት በሚሰዋ መሥዋዕት ደስ አላለህም። በዚያን ጊዜ፦ እነሆ፥ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ አልሁ ይላል። ዕብራውያን 10፡5-7
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos
#የእግዚአብሄርምክር #የእግዚአብሔርፈቃድ #እግዚአብሔር #እንደተፃፈ #ማታዘዝ #መባ #መሥዋዕት ##እምነት #የሰውአሳብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ
No comments:
Post a Comment