Popular Posts

Saturday, July 8, 2023

የፆታ ግንኙነቱ ዋና ዓላማ

 


እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት። እግዚአብሔር አምላክም የምድር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ሁሉ ከመሬት አደረገ፤ በምን ስም እንደሚጠራቸውም ያይ ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳምም ሕያው ነፍስ ላለው ሁሉ በስሙ እንደ ጠራው ስሙ ያው ሆነ። አዳምም ለእንስሳት ሁሉ፥ ለሰማይ ወፎችም ሁሉ፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ ስም አወጣላቸው፤ ነገር ግን ለአዳም እንደ እርሱ ያለ ረዳት አልተገኘለትም ነበር። እግዚአብሔር አምላክም በአዳም ከባድ እንቅልፍን ጣለበት፥ አንቀላፋም፤ ከጎኑም አንዲት አጥንትን ወስዶ ስፍራውን በሥጋ ዘጋው። እግዚአብሔር አምላክም ከአዳም የወሰዳትን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት፤ ወደ አዳምም አመጣት። አዳምም አለ፦ ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት፥ ሥጋም ከሥጋዬ ናት፤ እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል። ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፥ በሚስቱም ይጣበቃል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። ዘፍጥረት 218-24

እግዚአብሔር ወንድና ሴትን የፈጠራቸው ለአለመው የፆታ ግንኙነት እንዲስማሙ አድርጎ ነው፡፡ እግዚአብሔር ለወንድ ሴትን ከመፍጠሩ በፊት ብዙ እይነት እንስሳትን በፊቱ አሳልፎለት ነበር፡፡ ሰው ግን "ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት ሥጋም ከሥጋዬ ናት" ብሎ ለፆታ ግንኙነት የተቀበለው ከጎኑ የወጣችውን ሴት ብቻ ነበር፡፡

"ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም" የሚለውን የእግዚአብሔርን የቤተሰብ እቅድ ለማስፈፀም የወንድ እና የሴት የፆታ ግንኙነት ወሳኝ ነው፡፡

እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው። ዘፍጥረት 1፡28

እግዚአብሔር በወንድ እና በሴት ውስጥ እግዚአብሔር ያየው የቤተሰብ እቅድ ግብ እንዲመታ ወንድ ያለሴት ሴትም ያለወንድ አይሆንም፡፡ እግዚአብሔር ለቤተሰብ ስኬት የሚያስፈለግውን ነገር ሁሉ በወንድ እና በሴት ውስጥ አስቀምጧል፡፡

ወንድ እግዚአብሔር በህይወቱ ያለመውን የፆታ ግንኙነት እቅድ የሚያሳካው በምትመቸው ረዳት ሴት ብቻ ነው፡፡ ሰውም ለፆታዊ ግንኙነት አላማ የተፈጠረው ለዚሁ የእግዚአብሔር የጥንቱ /ኦርጅናል/ እቅድ መሳካት ነው፡፡

ወደድንም ጠላንም ሰው በቤተሰብ ፍሬያማ የሚሆነው በተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ብቻ ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

 #ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ፍቅር #ተቃራኒፆታ #ወንድ #ሴት #ወንድእናሴት #ተመሳሳይፆታ #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ትዳር


No comments:

Post a Comment