እግዚአብሔር
አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም
ብሎ ጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 5፡1-2
እግዚአብሔር
ሰውን የፈጠረው በመልኩና በአምሳሉ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው
ሙሉ ለሙሉ በምድር ላይ እንዲወክለው ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሙሉ ምስል የሚገለጠው በተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ውስጥ ነው፡፡ በቤተሰብ
አንድ ፆታ ብቻ የእግዚአብሔርን ከፊል መልክ እንጂ ሙሉ መልክ ሊያንፀባርቅ አይችልም፡፡ የእግዚአብሔርን የተሟላ መልክ ለማንፀባረቅ
ወንድ እና ሴት ያስፈልጋሉ፡፡
የተቃራኒ
ፆታ ግንኙነትን መቃወም የእግዚአብሔርን መልክ መቃወም ነው፡፡ የተቃራኒ ፆታ ግንኙነትን መጣል የእግዚአብሔርን ሙሉ መልክ መጣል
ነው፡፡
የተቃራኒ
ፆታ ግንኙነት በዝምታ ስለ እግዚአብሔር ህልውና ይናገራል፡፡
የተቃራኒ
ፆታ ግንኙነትም መቃወም እና ማንኛውንም ሌላ አማራጭ ማምጣት የእግዚአብሔርን መልክ ከምድር ላይ እንደማጥፋት ይቆጠራል፡፡
እግዚአብሔር
አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም
ብሎ ጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 5፡1-2
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ኢየሱስ
#ጌታ #ጋብቻ
#ፍቅር #ተቃራኒፆታ
#ወንድ #ሴት
#ወንድእናሴት #ተመሳሳይፆታ #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር
#ትዳር
No comments:
Post a Comment