Popular Posts

Tuesday, July 11, 2023

የተቃራኒ ፆታ ግንኙነት የተፈጥሮ ባህሪን ያለመከተል ጣጣ


ተፈጥሮ ፍፁም ነው፡፡ ተፈጥሮ ሁሉንም ያሟላል፡፡ ተፈጥሮን የሚያስተምረውን ከተከተልን ከብዙ ጉድለት እና ጥፋት እንጠበቃለን፡፡

ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን? 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፡14-15

ነገር ግን አንዴ ተፈጥሮን አንከተለም ብለን ካመፅን ጣጣው ብዙ ይሆናል፡፡

ተፈጥሮን ካልተከተልን በስተቀር ተፈጥሮ የምታዘጋጀውን ነገር ሁሉ እንጥላለን፡፡ ተፈጥሮን ካልተከተለን ተፈጥሮ የምትሰጠውን ነገር በራሳችን ማሟላት ይጠበቅብናል፡፡ ተፈጥሮን ካልተከተልን ተፈጥሮ የምታሟላውን ነገር በራሳችን ማሟላት ስለማንችል ከብዙ ነገር እንጎድላለን፡፡

አንዴ ደግሞ ተፈጥሮን ንቀን ሌላ ምርጫ ከመረጥን እንደገና ወደተፈጥሮ ለመመለስ እስካልወሰንን ድረስ ሁለንተናችን ይዛባል፡፡

ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። ወደ ሮሜ ሰዎች 1፡26-27

ተፈጥሮአዊ ባህሪውን ተቃውሞ በሰላም የሚኖር ወይም ወደአሰበበት ግብ የሚደርስ ማንም ሰው የለም፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

 #ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ፍቅር #ተቃራኒፆታ #ወንድ #ሴት #ወንድእናሴት #ተመሳሳይፆታ #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ትዳር

 

No comments:

Post a Comment