Popular Posts

Thursday, July 27, 2023

በአንድ አሳብ ተስማሙ

 


በአንድ አሳብ ተስማሙ፥ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 22-3

በአንድ አሳብ ተስማሙ የሚለው ትእዛዝ ለአእምሮ የሚከብድ ትእዛዝ ነው፡፡ እግዚአብሔር ግን የማይቻል ትእዛዝ አያዘንም፡፡ በአንድ አሳብ መስማማት ይቻላል፡፡

በአንድ አሳብ ተስማሙ የሚለው ትእዛዝ የሚከብደን እኛ ጋር እውነት እንሰዳለ ስለሚመስለን እና አንድ ለመሆን እውነትን መተው እንዳለብን ስለሚመስለን ነው፡፡

ለአንድነት እውነትን መተው ትክክል አይደለም፡፡ ለአንድነት እውነትን መተው ማመቻመች እንጂ አንድነት አይደለም፡፡

በአንድ አሳብ መስማማት ማለት በእኔ ውስጥ አሳብ እንደመጣ ሁሉ በሌላው ሰው ውስጥ አሳብ ሎመጣ ይችላል ብለን የሌላውን አሳብ መቀበል ማለት ነው፡፡ በአንድ አሳብ የምንስማማው በሌላው ሰው አሳብ ተማምነን ሳይሆን "ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት" ላይ ተማምነን ነው፡፡

እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም፤ እርስ በርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፤ በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ። በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡1-5

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa


No comments:

Post a Comment