Popular Posts

Saturday, July 15, 2023

በአንድነት ደስታዬን ፈፅሙልኝ


በክርስቶስም አንዳች ምክር ቢሆን፥ የፍቅር መጽናናት ቢሆን፥ የመንፈስ ኅብረት ቢሆን፥ ምሕረትና ርኅራኄ ቢሆኑ፥ ደስታዬን ፈጽሙልኝ፤ በአንድ አሳብ ተስማሙ፥ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2:1-2

ሃዋርያው ጳውሎስ ደስታዬን ፈፅሙልኝ በማለት የቅዱሳን #አንድነት ደስታው እንደሆነ ይናገራል፡፡ የቤተክርስትያን አንድነት የጳውሎስ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርም ደስታ ነው፡፡ የጳውሎስ ደስታ የእግዚአብሔር  ደስታ ነፀብራቅ እንጂ የራሱ የግሉ ደስታ አይደለም፡፡

እግዚአብሔር በአንድነታችን ደስ ይለዋል፡፡ ካለ አንድነት መንግስቱ ሊያሸንፍ አይችልም፡፡ ካለ አንድነታችን እግዚአብሔር በምድር ላይ ሊሰራ ያሰበውን ስራ መስራት አይችልም፡፡ ካለአንድነታችን ፈቃዱን በምድር ማድረግ አይችልም፡፡

የልጆቹ አንድነት የእግዚአብሔር የዘወትር የልብ ጩኸት ነው፡፡ እግዚአብሔር በህይወታችን ማየት የሚፈልገው የልብ መሻቱና ፍላጎቱ አንድነታችን ነው፡፡

እግዚአብሔርን ከሚያረኩት እና ከሚያስደስቱት ነገሮች አንዱ የእኛ አንደነት ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር

 

No comments:

Post a Comment