Popular Posts

Wednesday, July 5, 2023

ስለተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ወንድ እና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው


እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 5፡1-2

የጥንቱን የመጀመሪያውን ኦሪጅናሉን የእግዚአብሔርን ሃሳብ መረዳት ከብዙ ጥፋት ያድናል፡፡

እውቀት ከማጣት የተነሳ የእግዚአብሔር እውነት የሌለው ሰው ከመንገድ በመሳት ከህይወት ይጠፋል፡፡

ሰው የተፈጠረበትን የተቃራኒ ፆታ ግንኙነት አላማ ትክክለኛ እይታ ወይም ራእይ ከሌለው መረን ይወጣል፡፡

ራእይ ባይኖር ሕዝብ መረን ይሆናል፤ ሕግን የሚጠብቅ ግን የተመሰገነ ነው። መጽሐፈ ምሳሌ 29፡18

አሁን በአለማችን ላይ የምናያቸው በተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ላይ ያሉ ግራ መጋባቶች የእግዚአብሔርን ሃሳብ ካለመረዳት የመነጩ ናቸው፡፡ ሰዎች እግዚአብሔር እንዴት እንደፈጠራቸው ካልተረዱ ህይወታቸውን አላግባብ ያባክኑታል ያልተፈጠሩበትን አላማ ለማሳካት ሲሞክሩ በዘመናቸው ሁሉ ሲሰቃዩ ይኖራሉ፡፡

ለተፈጠረበት ልዩ አላማ እንጂ እንደ ምርጫችን ለፈለግንበት አላማ እንድንጠቀምበት የተፈጠረ የአካል ክፍል የለንም፡፡ የሰው እያንዳንዱ የአካል ክፍሉ የተፈጠረው በጥንቃቄ በተፈጠረበት አላማ ላይ ብቻ እንዲውል ነው፡፡ ሰው ታዲያ በሞኝነት ከተፈጠረበት አላማ ውጭ አካሌን ለፈለግኩት አላማ እጠቀምበታልሁ ሲል አካሉን ያለአግባብ ያጎሳቁለዋል፡፡

ህይወትን ከማጎሳቆል እና ከማበላሸት የምንጠበቀው የፈጠረንን የእግዚአብሔርን አላማ ስንከተል ብቻ ነው፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

  #ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ፍቅር #ተቃራኒፆታ #ወንድ #ሴት #ወንድእናሴት #ተመሳሳይፆታ #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ትዳር  

 

No comments:

Post a Comment