Popular Posts

Friday, July 28, 2023

አንድነት ሌላው እንደራስ መቀበልን ይጠይቃል

 

የእይታ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር አብዛኛውን ጊዜ አብዛኛው ሰው የሚያቀርበው አሳብ ከእኛ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ አብዛኛዎቹ የሚያስቡት እኛም በእነርሱ ሁኔታ ብንሆን የምናቀርበውን ተመሳሳይ አሳብ ነው፡፡  ታዲያ አንዳችን የአንዳችንን አሳብ እንዳንቀበል እና እንዳንተገብር የሚያደርገን የእይታ እጥረት ብቻ ነው፡፡ አንዳችን በአንዱ አሳብ መስማማት የማንችለው የራሳችንን አሳብ ብቻ ቅዱስ የሌላውን ሰው ሁሉ አሳብ እርኩስ የማድረግ ዝንባሌ ሲኖረን ነው፡፡

አሳባችንን ካቀረብን በኋላ ህሊና ያለው ሰው ይቀበለናል ብለን በራሳችን አሳብ ሃያልነት ማመን አለብን፡፡ ሰው ካልተቀበለው ደግሞ ዛሬ የተቀበሉት ሌላ የተሻለ አሳብ አለ ብለን ማመን ግድ ነው፡፡ ሁልጊዜ የራሱ አሳብ ተቀባይነት ካላገኘ አንድነትን ለማፍረስ ግድ የማይለው ሰው የአንድነት ጠላት ነው፡፡

እኛ ብቻ ህሊና እንዳለን ሌላው ሰው ሁሉ ህሊና እንደሌለው ማሰብ መጀመር የአንድነት ጠላት ነው፡፡ ከላእኛ በስተቀር ሌላውን ሁሉ እርኩስ ማድረግ የመከፋፈል የመጀመሪያው እርምጃ ነው፡፡

አንድነት የልብ ስፋት ይጠይቃል፡፡ አንድነት በሌላው አሳብ የመመራት እምነት ይጠይቃል፡፡ አንድነት በራስ መተማመን ይጠይቃል፡፡ አንድነት በሌላው አሳብ ማመን ይጠይቃል፡፡ አንድነት በራስ አሳብ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ህይወት ውስጥ የእግዚአብሄርን አሰራር መረዳትን ይጠይቃል፡፡

ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፡5

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር


No comments:

Post a Comment