Popular Posts

Friday, July 7, 2023

የተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ንድፍ

 


ሰውን የፈጠረው እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው በአላማ ነው፡፡  እግዚአብሔር ሰውን ከመፍጠሩ በፊት ምን አይነት የፆታ ግንኙነት ሊኖረው እንደሚችል ያውቅ ነበር፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ሁለንተና የፈጠረው ለዚያ ላቀደው የፆታ ግንኙነት እንዲስማማ አድርጎ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረበትን የመጀመሪያ እቅዱን ማወቅ ሰው ለታቀደለት አላማ እንዲኖር ይረዳዋል፡፡ ሰው የመጀመሪያ ካርታውን ካላገኘ ለምን እንደተፈጠረ ግራ ስለሚገባው ባልተፈጠረበት አላማ ላይ ህይወቱን ያባክናል፡፡

እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አለ፦ ፈጣሪ በመጀመሪያ ወንድና ሴት አደረጋቸው፥ የማቴዎስ ወንጌል 19፡4

አዲስ እቃ ስንገዛ ሁልጊዜ እቃው ማኑዋል ይኖረዋል፡፡ ማኑዋሉ ስለእቃው ስለእቃው አለማ እና አጠቃቀሙ መመሪያን ይሰጣል፡፡ ከመጠቀማችሁ በፊት የእቃውን መመሪያ /ማኑዋሉን/ እንብቡ የሚል ምክር ያለበት የምናነበው ስለዚህ ነው፡፡ ሰው ከሰራው ግለሰብ የእቃውን  አጠቃቀም ካልተረዳ በስተቀር አላግባብ ሊጠቀምበት ይችላል፡፡ ሰው እቃውን አላግባብ ካጎሳቆለው እና ላልተሰራበት አላማ ካዋለው ያበላሸዋል እንዲሁም የሚፈለገውን ውጤት አያገኝም፡፡

እንዲሁም ለምን እንደተፈጠርን በትክክል የምንረዳው እኛን ከፈጠረን ከእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ስለአሰራራችን እና አጠቃቀሙ ከእግዚአብሔር ካልተረዳን ሌላ ማንም ሰው ስለአጠቃቀሙ በትክክል ሊያስረዳን አይችልም፡፡

ስለተቃራኒ ፆታ ግንኙነታችን ሊነግረን የሚችለው እውነተኛውን እውቀት ሊሰጠን የሚችለው ያበጃጀን እና የሰራን የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው፡፡ እውነተኛው የህይወት መመሪያችን ሊሆን የተገባው የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡

የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3፡16-17

ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ የምንሄደው ማንኛውም አካሄድ ተፈጥሮአችንን እና ስሪታችንን ያጎሳቁለዋል፡፡   

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa 


No comments:

Post a Comment