Popular Posts

Tuesday, July 4, 2023

የተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ትኩረት


ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ መፅሃፍ ቅዱስ በተለይ ስለተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ምን እንደሚያስተምር በአጭሩ ለመመለከት ነው፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ አሁን በአለማችን ላይ ስላለው የፆታ ግንኙነት ግራ መጋባት ምን እንደሚል እንመለከታለን፡፡  

ከተቃራኒ ፆታ ውጭ ስላለው ግንኙነት ተዘርዝሮ አያልቅም፡፡ እውነት አንድ ነው፡፡ ውሸት ግን ስፍር ቁጥር የለውም፡፡ እውነትን ለመረዳት እውነትን ብቻ አበጥሮ መፈተሽ ይጠቅማል እንጂ ተቆጥሮ የማያልቀውን ተፈብረኮ የማያባራውን ውሸትን ለመረዳት መሞከር ብክነት ነው፡፡

የገንዘብ መቁጠሪያ ማሽን ባልነበረበት ጊዜ የባንክ ሰራተኞች የተሳሳተውን የባንክ ኖት እንዳይቀበሉ በእውነተኛው የባንክ ኖት ላይ ሰፊ ስልጠና ይሰጣቸው ነበር፡፡ በየቀኑ ተፈብርኮ የማያልቀውን በየቤቱ የሚሰራውን የተሳሳተ ኖት በማጥናት ውድ ጊዜያቸውን አያባክኑም ነበር፡፡ እውነተኛውን የብር ኖት ጠንቅቆ የተረዳ ሰው ግን የተሳሳተ የባንክ ኖት ሲመጣ ከትክክለኛው የባንክ ኖት እንፃር አስተያይቶ ስህተቱን በቀላሉ ይለየዋል፡፡

አሁንም የእግዚአብሄር ስለተቃራኒ ፆታ ግንኙነት የሚናገረውን መረዳት የተሳሳተ ማንኛውም አይነት ግንኙነት በየጊዜው ቢመጣ ስህተቱ በቀላሉ ይታወቃል፡፡

ስለማንኛውም ነገር ክርክር ቢነሳ የጥንቱን ኦርጂናሉን ነገር ማግኘት የክርክር ፍፃሜን ያደርጋል፡፡  

ስለፆታ ግንኙነት ጥያቄ በተነሳ ጊዜ ኢየሱስ የመለሰው ይህንን ነበር፡፡  

ከጥንት ግን እንዲህ አልነበረም። የማቴዎስ ወንጌል 19፡8

በተቃራኒ ፆታ ግንኙነት የእግዚአብሔርን ኦሪጅናል ሃሳብ በሚቀጥሉት ፅሁፎች እንመለከታለን፡፡

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

  #ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ፍቅር #ተቃራኒፆታ #ወንድ #ሴት #ወንድእናሴት #ተመሳሳይፆታ #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ትዳር 


 

No comments:

Post a Comment