የእግዚአብሔር
ፍፁም ፈቃድ አንድነታችን ነው፡፡
ሁሉም
አንድ ይሆኑ
ዘንድ፥ ከቃላቸው
የተነሣ በእኔ
ስለሚያምኑ ደግሞ
እንጂ ስለ
እነዚህ ብቻ
አልለምንም፤ አንተ
እንደ ላክኸኝ
ዓለም ያምን
ዘንድ፥ አንተ፥
አባት ሆይ፥
በእኔ እንዳለህ
እኔም በአንተ፥
እነርሱ ደግሞ
በእኛ አንድ
ይሆኑ ዘንድ
እለምናለሁ። እኛም
አንድ እንደ
ሆንን አንድ
ይሆኑ ዘንድ፤
እኔም በእነርሱ
አንተም በእኔ
ስትሆን፥ በአንድ
ፍጹማን እንዲሆኑ፥
የሰጠኸኝን ክብር
እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤
እንዲሁም ዓለም
አንተ እንደ
ላክኸኝ በወደድኸኝም
መጠን እነርሱን
እንደ ወደድሃቸው
ያውቃል። የዮሐንስ
ወንጌል 17፡11፡20-23
ኢየሱስ
የፀለየው የእግዚአብሔርን
ፈቃድ ስለሆነው
ስለ አንድነታችን ነበር፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ "እንደ ፈቃዱ
አንዳች ብንለምን ይሰማናል" እንደሰማን ካወቅን እንደሚመልስ እናውቃለን እንደሚል የኢየሱስ በአብ ፀሎት ተሰምቷል ተመልሷልም፡፡
በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን። 1ኛ የዮሐንስ
መልእክት 5፡14-15
በኢየሱስ
ፀሎት ወደጥንቱ እና እግዚአብሔር በመጀመሪያ ወደ አቀደው ወደ አንድነታችን ተመልሰናል፡፡
አንድ ነን፡፡
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ኢየሱስ
#ጌታ #አንድ
#ፍቅር #አንድነት
#ህብረት #አካል
#ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር
No comments:
Post a Comment