በአንድ አሳብ ተስማሙ፥ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡2-3
አንድነት
የሚኖረው ሌላው የሌለውን ፍላጎት ልናሟላ ከመጣን ብቻ ነው፡፡ የራሱን ጥቅም ብቻ የሚያይ ችእና ለሌላው ጥቅም እውቅና የማይሰጥ
ሰው አንድነት ሊያመጣ አይችልም፡፡ ሰው በተፈጥሮው አድልዎ ሊኖርበት ይችላል፡፡ ሰው በተፈጥሮው ወገናዊ ሊሆን ይችላል፡፡
አድልዎ
አንድነትን ያፈርሳል፡፡ አንዱን ከሌላው ከፍ አድርጎ ማየት የአንድነት ጠር ነው፡፡ አንዱን ከሌላው ዝቅ አድርጎ ማየት አንድነትን
ይንዳል፡፡ ለሌላው ማድላት አንድነትን አያመጣም፡፡ ሌላውን መናቅ እና መጥላት አንድነት ያበላሻል፡፡
አድልዎን
ማስወገድ ሰውን በእኩልነት ማየት አንድነትን ይገነባል፡፡ ሌላውን እንደራስ ማየት አንድነትን ይፈጥራል፡፡ ሌላውን በሰውነቱ መቀበል
አንድነትን ያጠናክራል፡፡ በመከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነት ብቻ ፅኑ መሰረት አለው፡፡
በአንድ
አሳብ ተስማሙ፥ አንድ ፍቅር አንድም ልብ አንድም አሳብ ይሁንላችሁ፤ ለወገኔ ይጠቅማል በማለት ወይም በከንቱ ውዳሴ ምክንያት አንድ
እንኳ አታድርጉ፥ ነገር ግን እያንዳንዱ ባልንጀራው ከራሱ ይልቅ እንዲሻል በትሕትና ይቍጠር፤ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፡2-3
#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
No comments:
Post a Comment