“አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ
ተጠበቁ፥ እርሱም
ግብዝነት ነው።”
የሉቃስ ወንጌል
12፡1
ኢየሱስ በምድር ላይ በተመላለሰበት ጊዜ ፈሪሳዊያን
ሰዲቃዊያን እና ጻፎች የሚባሉ የሃይማኖት መሪዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ የሃይማኖት መሪዎች የእግዚአብሔርን ነገር የሚያስቀድሙ መንፈሳዊ
መሪዎች አልነበሩም፡፡ ይልቁንም መንፈሳዊ አይታ የጠፋባቸው በመንፈሳዊ ነገር ምትክ የአምልኮት መልክ ብቻ የነበራቸው ነበሩ፡፡
ፃፎች እና ፈሪሳዊያን የሃይማኖቱ አላማ የጠፋባቸው
በእውነተኛው አምልኮ ምትክ የውጫዊ ስርአትን የተኩ እና ይህ ነው ሃይማኖት ብለው ለመማርም ብሎም ለመለወጥም ያልተዘጋጁ ሰዎች ነበሩ፡፡
እነርሱብ በተመለከተ ሰው ውጫዊውን ነገር ከጠበቀ ውስጣውን የልብ ህይወቱን ንፁህ ማድረግ አይጠበቅበትም ነበር፡፡ ለእነርሱ ሃይማኖት
የውጭ ትእይንት ብቻ ነበር፡፡
እነዚህ የሃይማኖት መሪዎች የውስጥ የልብ ነገራቸውን
ስለረሱት ማተኮር ያለባቸው በልብ ነገር ላይ እንደሆነ ኢየሱስ ይናገራቸው ነበር፡፡
ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ እናንተ ደግሞ እስካሁን የማታስተውሉ ናችሁን? ወደ አፍ የሚገባ ሁሉ ወደ ሆድ አልፎ ወደ እዳሪ እንዲጣል አትመለከቱምን? ከአፍ የሚወጣ ግን ከልብ ይወጣል፥ ሰውንም የሚያረክሰው ያ ነው። ከልብ ክፉ አሳብ፥ መግደል፥ ምንዝርነት፥ ዝሙት፥ መስረቅ፥ በውሸት መመስከር፥ ስድብ ይወጣልና። ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው እንጂ፥ ባልታጠበ እጅ መብላትስ ሰውን አያረክሰውም። የማቴዎስ ወንጌል 15፡16-20
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ
Abiy Wakuma Dinsa
#ኢየሱስ #ጌታ #ፈሪሳውያን
#ግብዝነት #የአምልኮትመልክ
# #ጻፎች #ቤተክርስቲያን
#መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ሰዱቃውያን
No comments:
Post a Comment