Popular Posts

Sunday, July 9, 2023

የፆታዊ ግንኙነት እና ልጆች

 

ሰው የተፈጠረው ለፆታዊ ግንኙነት ነው፡፡ እግዚአብሔር ለወንድ የፆታ ግንኙነት ሴትን ፈጠረእግዚአብሄር ወንድን ለሴት ሴትን ደግሞ ለወንድ እንድትመች አድርጎ መቅረፁ ብቻ ደግሞ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ወንድና ሴት ለልጆች አስተዳደግ እንዲመቹ አድርጎ አዘጋጅቶም ነው፡፡

አንድ ልጅ ወደአለም የሚመጣው እጅግ በተቀራረበ የወንድና የሴት የፆታ ግንኙነት መካከል ነው፡፡ እግዚአብሔር በዚህ እጅግ የተቀራረበ የወንድ እና የሴት ግንኙነት መካከል ብቻ ልጅ እንዲፈጠር ያደረገበት ምክኒያት ልጆች ማደግ ያለባቸው በወንድ እና በሴት አባትነት እና እናትነት ጥላ ስር ስለሆነ ነው፡፡

አንድ ልጅ ሙሉ ሰው ለመሆን በዋነኝነት የወንድ እና የሴት አስተዋፅኦ ያስፈልገዋል፡፡ ከአባት ጥንካሬን ስርአትን መሪነትን ሃላፊነትን ሲካፈል ከሴት ደግሞ ርህራሄን ፍቅርን እንክብካቤን በዋነኝነት ይካፈላል፡፡ ታዲያ ልጅ በወንድ እና በሴት ባህሪያት በሙሉ ካልተገነባ ሙሉ ሰው መሆን አይችልም፡፡ በወንድ እና በወንድ መካከል ያደገ ልጅ የእናት አስተዋፅኦ የሆኑት ርህራሄ ፍቅርን እንክብካቤ ይጎድለዋል፡፡ በሴት እና በሴት መካከል ያደገ ልጅ ጥንካሬን ስርአትን መሪነትን ሃላፊነት መሸከም ስለሚጎድለው ሙሉ ሰው መሆን ያቅተዋል፡፡

እግዚአብሔር ሰውን ወንድ እና  ሰሴት አድርጎ ለፆታ ግንኙነት የፈጠረው የወንድ እና የሴት ባህሪ ስለሚያስፈልግ ነው፡፡ እግዚአብሔር ልጆች በአባትና በእናት መካከል እንዲወለዱ እና እንዲያድጉ ያቀደው የወንድ እና የሴትን ባህሪ ተካፍለው ሙሉ ሰው ሆነው እንዲያድጉ ነው፡፡

እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 5፡1-2

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

 #ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ፍቅር #ተቃራኒፆታ #ወንድ #ሴት #ወንድእናሴት #ተመሳሳይፆታ #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ትዳር


No comments:

Post a Comment