Popular Posts

Tuesday, July 25, 2023

አንድነት ከፍቅር ይመነጫል

 

መለያየት ከመምጣቱ በፊት ቀድሞ የሚመጣው ጥላቻ ነው፡፡ መለያየት ከመምጣቱ በፊት ቀድሞ የሚመጣው ንቀት ነው፡፡ ከምትጠላው ሰው ጋር አንድ ልትሆን አትችልም፡፡ ከምትንቀው ሰው ጋር አንድ ልትሆን አትችልም፡፡ ለጊዜው ልታስመስል ትችላለህ ነገር ግን ለሌላው ያለህን ንቀት እና ጥላቻን ልትደብቀው ግን አትችልም፡፡

አንድነት ከመቀበባል ይመነጫል፡፡ አንድነት ሰውን በማንነቱ ከመቀበል ይመነጫል፡፡ አንድነት ሰውን በእግዚአብሔር ፍጡርነቱ ከመቀበል ይጀምራል፡፡ አንድነት ሌላው በእግዚአብሔር መወደዱን ከመረዳት ይመነጫል፡፡ አንድነት ሰውን እግዚአብሔር እንደሚያየው ከማየት ይመጣል፡፡ አንድነት እግዚአብሔር እርሱን ከሃጢያት ጥፋት እና ለዘላለም ከእግዚአብሔር ጋር ከመለያየት ለማዳን ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን  እንደላከለት ከማየት ይመነጫል፡፡

አንድነት ሰው በክርስቶስ ያለውን የክብር ዋጋ ከመረዳት ይመነጫል፡፡ አንድነት ሰውን እግዚአብሔር በክርስቶስ እንደሚያየው ከማየት ይመጣል፡፡

ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5፡16

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa


No comments:

Post a Comment