Popular Posts

Thursday, July 6, 2023

የተቃራኒ ፆታ ግንኙነት ጅማሬ

 



ሰው በድንገት በምድር ላይ የተገኘ ፍጡር አይደለም፡፡ ሰው በእግዚአብሔር የተፈጠረ ባለቤት እና አስተዳዳሪ ያለው ፍጡር ነው፡፡

እግዚአብሔር ደግሞ የአላማ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ከመፍጠሩ በፊት ምን አይነት የፆታ ግንኁነት እንደሚኖረው ወስኖ ነበር፡፡

የሰውን የፆታ ግንኁነት አላማ ገና ከመፈጠሩ በአፈጣጠሩ እቅድ ውስጥ በግልፅ የምንመለከተው ስለዚህ ነው፡፡

እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 5፡1

እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው በመልኩ እና በአምሳሉ ነው፡፡ ወንድ እና ሴት ናቸው የእግዚአብሔርን መሉ መልክ እና አምሳል መግለጥ የሚችሉት ወንድ እና ሴት ናቸው፡፡ ወንድ ብቻውን ወይም ሴት ብቻዋን የእግዚአብሔርን መልክ ሊያንፀባርቁ አይችሉም፡፡ የእግዚአብሔርን ሙሉ መልክ ለመግለፅ ወንድ እና ሴት ይጠይቃል፡፡ እግዚአብሔር በመልኩ የፈጠረውን ሰው ወንድ እና ሴት አድርጎ የፈጠረው ለዚህ ነው፡፡

ወንድ የሚገልፀው ጥላ መሆንን ፣ ቀዳሚነትን ፣ መሪነትን ፣ ጥንካሬን ፣ ስርአት ማስያዝን እና የመሳሰሉትን የእግዚአብሔርን የወንድነት ባህሪ ነው፡፡

ሴት እንዲሁ የምትገልፀው ምህረትን ርህራሄን እንክብካቤን ልስላሴን ምቾትን እና የመሳሰሉትን የእግዚአብሔርን የሴትነት ባህሪያት ነው፡፡

አንድ ቤተሰብ በባል እና በሚስት አማካኝነት እነዚህን የወንድ እና የሴት ባህሪያትን በመግለፅ የእግዚአብሔርን መልክ እና አምሳል በምድር ላይ በሙላት ይገልፃሉ፡፡

እግዚአብሔር አዳምን በፈጠረ ቀን በእግዚአብሔር ምሳሌ አደረገው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፥ ባረካቸውም። ስማቸውንም በፈጠረበት ቀን አዳም ብሎ ጠራቸው። ኦሪት ዘፍጥረት 5፡1-2

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

#ኢየሱስ #ጌታ #ጋብቻ #ፍቅር #ተቃራኒፆታ #ወንድ #ሴት #ወንድእናሴት #ተመሳሳይፆታ #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #ትዳር


No comments:

Post a Comment