Popular Posts

Wednesday, July 19, 2023

አንድነትን የምንፈራው

 

ብዙ ሰው አንድ ለመሆን ይፈራል፡፡ የአንድነትን አሳብ በጥርጣሬ ይመለከተዋል፡፡

ብዙ ሰው አንድ ለመሆን የሚጠላበት ዋናው ምክኒያት አንድነትን ስለሌላው አሳብ የራስን አሳብ መጣል እንደሆነ ፣ አንድነት ስሌላው ፍላጎት የራስን ፍላጎት መተው እንደሆነ እና አንድነት ስለሌላው መረዳት የራስን መረዳት መተው እንደሆነ አድርጎ ስለሚወስደው ነው፡፡

እርግጥም አንዳንድ ሰዎች አንድነት የሚሉት ፍፁም የተሳሳተ አንድነት ነው፡፡ አንዳንዶች አንድነት አንድነት የሚሉት ለራሳቸው ጥቅም ስለማመቻቸት ብቻ እንጂ እውነተኛውን አንድነት ተረድተውትም አይደለም፡፡

እውነተኛው አንድነት ያስደስታል እንጂ አያስፈራም፡፡ እውነተኛው አንድነት ያኮራል እንጂ አያሸማቅቅም እውነተኛው አንድነት ፍሬያማ ያደርጋል እንጂ አያቀጭጭም፡፡ እውነተኛው አንድነት ያጠነክራል እንጂ አያደክምም፡፡

ማስመሰያው አንድነት ያለው እውነተኛው አንድነት ስላለ ነው፡፡ ማስመሰያው አንድነት አለ ማለት እውነተኛው አንድነት የለም ማለት አይደለም፡፡ እንዲያውም ማስመሰያው አንድነት ካለ እውነተኛው አንድነት እንዳለ ማረጋጋጫው ነው፡፡ እውነተኛ ነገር ከሌላ የእርሱ ርካሽ ማስመሰያ አይሰራምና፡፡

በብርቱ ይፈልጉአችኋል፥ ለመልካም አይደለም ነገር ግን በብርቱ ትፈልጉአቸው ዘንድ በውጭ ሊያስቀሩአችሁ ይወዳሉ። ወደ ገላትያ ሰዎች 4፡17

እውነተኛውን አንድነት መረዳት እና ራሳችንን መስጠት እንጂ ስለተሳሳተው የአንድነት አሳብ አንድነትን መፍራት የለብንም፡፡

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa


No comments:

Post a Comment