Popular Posts

Sunday, July 23, 2023

አንድነት ሳይሆን ተመሳሳይነት ርካሽ ነው

 

አንድነት ሳይሆን ተመሳሳይነት ርካሽ ነው

አንድነት የተመሳሳይነትን ሙከራ አውጥቶ ጥሎ በአላማ አንድነት ላይ ማተኮርን ይጠይቃል፡፡

ተመሳሳይነት ርካሽ ነው፡፡ የሚመስሉንን ሰዎች ብቻ መቀበል ብርቅ አይደለም፡፡ ማንም መንገደኛ የሚመስሉትን ሰዎች ይሰበስባል ከእነርሱም ጋር ሊተባበር ይችላል፡፡

አንዳንድ ሰው አንድነት የሚለው መከፋፈልን ነው፡፡ እኛን የማይመስሉንን ሰዎች አውጥቶ መጣል መከፋል እንጂ አንድነት አይደለም፡፡

ስለዚህ ከእኛ የተለየውን ሰው ከህይወታችን አውጥተን መጣል እንደ አንድነት ጥረትን የማይጠይቅ ቀላል ነገር ነው፡፡ ማንም ሰነፍ ከእርሱ የተለየውን ሰው ከፊቱ አውጥቶ ይጥላል፡፡ ተመሳሳይነት ብዙም ጥረት አይጠይቅንም፡፡ ተመሳሳይነት ቅፅበታዊ ነው፡፡

የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። የማቴዎስ ወንጌል 5፡46-48

አንድነት ግን ከመቀፅበት አይመጣም፡፡ አንድነት ለሰነፎች እና ለልፍስፍሶች አይደለም፡፡ አንድነት የልብ ስፋትን ይጠይቃል፡፡ አንድነት ማስተዋልን ይጠይቃል፡፡ አንድነት ትጋትን ይጠይቃል፡፡ አንድነት ፍቅርን ይጠይቃል፡፡  

#ኢየሱስ #ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa


No comments:

Post a Comment