እግዚአብሔርን
ያየው አንድም እንደሌለ ልጁ ኢየሱስ ብቻ እንደተረከው መፅሃፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ የእግዚአብሔርን ልብ የምናየው በኢየሱስ ክርስቶስ
አስተምህሮት እና ኑሮ ነው፡፡
በተለይ
በኢየሱስ ክርስቶስ ፀሎት የእግዚአብሔርን ልብ ፍንትው ብሎ ማየት እንችላለን፡፡ በተለይ ኢየሱስ በመጨረሻዎቹ የአገልግሎቱ ቀናት
የፀለየውን ፀሎት ስንመለከት ስለአንድነታችን የእግዚአብሔርን ልብ በግልፅ ማየት እንችላለን፡፡
ቅዱስ
አባት ሆይ፥ እነዚህን የሰጠኸኝን እንደ እኛ አንድ እንዲሆኑ በስምህ ጠብቃቸው። የዮሐንስ ወንጌል 17፡11
ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ ከቃላቸው የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑ ደግሞ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልለምንም፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ አንተ፥ አባት ሆይ፥ በእኔ እንዳለህ እኔም በአንተ፥ እነርሱ ደግሞ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ። እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ ስትሆን፥ በአንድ ፍጹማን እንዲሆኑ፥ የሰጠኸኝን ክብር እኔ ሰጥቻቸዋለሁ፤ እንዲሁም ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ በወደድኸኝም መጠን እነርሱን እንደ ወደድሃቸው ያውቃል። የዮሐንስ ወንጌል 17፡11፡20-23
በኢየሱስ አገልግሎት ትምህርቱም ፀሎቱም ስለእኛ አንድነት እንደነበር ከመፅሃፍ ቅዱስ
እንረዳለን፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
#ኢየሱስ
#ጌታ #አንድ #ፍቅር #አንድነት #ህብረት #አካል #ቤተክርስቲያን #መፅሐፍቅዱስ #ቃል #እግዚአብሔር #መተባበር
No comments:
Post a Comment