Popular Posts

Wednesday, June 7, 2023

በእግዚአብሔር የመመራት የመጀመሪያ እርምጃ


በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፤ መጽሐፈ ምሳሌ 3:5-7

በእግዚአብሔር ለመመራት ለእግዚአብሔር አምላክነት እውቅና መስጠት የመጀመሪያው እርምጃ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ለመመራት እግዚአብሔር ምድርን እየመራ እንደሆነ በሚገባ መረዳት ይጠይቃል፡፡ በእግዚአብሔር ምሪት ተጠቃሚ ለመሆን እግዚአብሔር በምድር ላይ እንድንሰራለት የሚፈልገው ልዩ ነገር እንዳለ እና ለህይወታችን ያለውን ፈቃዱን ሊያስረዳን እንደሚፈልግ ማመን አለብን፡፡

በእግዚአብሔር ለመመራት ከፈለግን በራሳችን ማስተዋል መመራትን ማቆም አለብን፡፡ የራሳችን ማስተዋል በቂ ቢሆን ኖሮ የእግዚአብሔርን ምሪት ባልፈለግን ነበር፡፡

በእግዚአብሔር አብልጠን መመራት ከፈለግን በመንገዳችን ሁሉ ለእርሱ ምሪት እውቅና መስጠት ይገባናል፡፡

እግዚአብሔር ስለሁሉም እንደሚመራን ካላወቅን በመንገዳችን ሁሉ እውቅና ልንሰጠው አንችልም፡፡ ዋና በምንላቸው ነገሮች ላይ ብቻ ለእርሱ ምሪት እውቅና ከሰጠን በምሪቱ ተጠቃሚ የምንሆነው በዋና ነገሮች ላይ ብቻ እንጂ በሁሉም የህይወታችን አቅጣጫ ላይ አይሆንም፡፡

በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፥ በራስህም ማስተዋል አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፥ እርሱም ጎዳናህን ያቀናልሃል። በራስህ አስተያየት ጠቢብ አትሁን፤ መጽሐፈ ምሳሌ 3:5-7

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa


No comments:

Post a Comment