እግዚአብሔርን የምንሰማባቸው ሶስት አይነት ድምፆች
ይገኛሉ፡፡ እግዚአብሔር በዋነኝነት በሶስት መንገዶች ለራሳችን ይናገረናል፡፡
የህሊና ድምፅ የውስጥ ምስክርነት የውስጥ ድምፅ እና የመንፈስ ቅዱስ ድምፅ በሚባሉ
ሶስት መንገዶች እግዚአብሔር በግል ሊመራን ይፈልጋል፡፡
ከእነዚህ ከሶስት አይነት ድምፆች እግዚአብሔር አብዛኛውን ጊዜ የሚመራን በውስጥ
ምስክርነት ነው፡፡ ይህ አይነት አመራር እኛ ራሳችን ጊዜ ወስደን በውስጣችን የምንፈልገው ምስክርነት እንጂ እግዚአብሔር በድምፅ
እንደሚናገረን የሚመጣልን ነገር አይደለም፡፡
የእግዚአብሔር
ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ወደ ሮሜ ሰዎች 8፡16
የውስጥ ምስክርነት ስለአንድ ነገር ስናስብ በልባችን የሚሰማን ምቾት ወይም መረበሽ
ነው፡፡ ይህ የአእምሮ ጉዳይ አይደለም፡፡ ነገር ግን በልባችን ውስጥ የምንሰማው እግዚአብሔር ስለምናስበው ነገር ያለውን አመለካከት
የምንለይበት መንገድ ነው፡፡
ስለአንድ ነገር ስናስብ በልባችም የሚቆረቁረን እና ምቾት የማይሰማን ከሆነ ነገሩ
ከእግዚአብሔር እንዳይደለ እንረዳለን፡፡ ስለእንድ ነገር ስናስብ ግን በልባችን ውስጥ ደስታ እና ምቾት የሚሰማን ከሆነ የእግዚአብሔር
ፈቃድ እንዳለበት እናስተውላለን፡፡
ይህ የውስጥ ምስክርነት ውሳኔ ከመወሰናችን በፊት በውስጣችን የምንፈልገው የእግዚአብሔር
የፈገግታ ፊት ወይም የተኮሳተረ ፊት ነው፡፡ ይህ አይነቱ ምስክርነት
በልባችን የምንፈልገው አደገኛ ነው የሚል ቀይ መብራት ወይም እለፍ የሚል አረንጓዴ መብራት ነው፡፡
እናንተ ሰዎች ሆይ፥ ይህ ጕዞ በጥፋትና በብዙ ጕዳት እንዲሆን አያለሁ፤ ጥፋቱም
በገዛ ሕይወታችን ነው እንጂ በጭነቱና በመርከቡ ብቻ አይደለም ብሎ መከራቸው። የሐዋርያት ሥራ 27፡10
ሁልጊዜ ይህንን ምስክርነት በልባችን ውስጥ የምንፈልግ እና አእምሮዋችንን ሳንሰማ
ታምነን የምንከተለው ከሆነ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንችላለን፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
No comments:
Post a Comment