Popular Posts

Tuesday, June 13, 2023

የመንፈስ ቅዱስ ድምፅ

 


እግዚአብሔር በመንፈሱ አማካኝነት ሊመራን ከሚፈልግባቸው መንገዶች ሶስቱ የውስጥ ምስክርነት ፣ የውስጥ ድምፅ እና የመንፈስ ቅዱስ ድምፅ ናቸው፡፡
የውስጥ ምስክርነት እግዚአብሔር በውስጣችን የሚሰጠን ምልክት ሲሆን ይህን ምልክት ራሳችን ፈልገን የምናገኘው ምልክት እንጂ ወደእኛ የሚመጣ ድምፅ አይደለም፡፡
የውስጥ ድምፅ ደግሞ መንፈስ እንደ ወደደ በውስጣችን የምንሰማው ድምፅ እንጂ ምስክርነት አይደለም፡፡
የመንፈስ ቅዱስ ድምፅ ጉልህ ድምፅ ነው፡፡ የውስጥ ድምፅን ከመንፈስ ቅዱስ ድምፅ የምንለየው የውስጥ ድምፅ በውስጣችን ራሳችን ብቻ የምንሰማው ሲሆን የመንፈስ ቅደስ ድምፅ ግን ጉልህ ድምፅ ከመሆኑ የተነሳ ሰው የጠራን ወይም የተናገረን ያህል ዞር ብለን የተናገረንን ሰው ልንፈልግ እንችላለን፡፡
እግዚአብሔር ሳሙኤልን ጠራው፤ እርሱም፦ እነሆኝ አለ። ወደ ዔሊም ሮጠ፦ እነሆኝ የጠራኸኝ አለው። እርሱም፦ አልጠራሁህም ተመልሰህ ተኛ አለው። ሄዶም ተኛ። መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 3፡4-5
ይህ የመንፈስ ቅዱስ ድምፅ እኛ ፈልገን የምናገኘው ድምፅ አይደለም፡፡
እኛም በቅዱሱ ተራራ ከእርሱ ጋር ሳለን ይህን ድምፅ ከሰማይ ሲወርድ ሰማን። 2ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፡18
በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ፦ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ ሰማ። የሐዋርያት ሥራ 9፡4
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

No comments:

Post a Comment