እግዚአብሔር
ሲፈጥረን እንድንሰማው አመቻችቶ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሲፈጥረን እርሱን የምንሰማበትን ነገር ሁሉ በውስጣችን አስቀምጦ ነው፡፡ እግዚአብሄርን
የምንሰማው እኛ ልዩ ሰሚዎች ስለሆንን ሳይሆን እርሱ በማሰማት የተካነ ተናጋሪ ስለሆነ ነው፡፡ እግዚአብሔርን መስማት በጣት ለጥቂት
ሰዎች አይደለም፡፡ እግዚአብሔርን መስማት የተሰጠው በክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሄር ጋር ለታረቁ ሁሉ ነው፡፡ እግዚአብሔርን መስማት
በክርስቶስ የመስቀል ስራ የእግዚአብሔር ልጆች ለሆኑ ሁሉ ነው፡፡
ለተቀበሉት
ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 1፡12
የፈጠረን
እግዚአብሄር እንዴት እንደሚናገረን ያውቃል፡፡ ፍጥረታችንን ሁሉ የሚያውቅ እግዚአብሔር እኛ እንድንረዳው አድርጎ መናገር አይሳነውም፡፡
እግዚአብሔር
በመናገር የተካነ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሲናገር እናውቃለን፡፡
የእኛ
የእግዚአብሔርን የመስማት ጥያቄ ከቁጥር የሚገባ አይደለም፡፡ ዋናው ነገር ፈቃዱን ለማድረግ እንወዳለን ወይ? የሚለውን ጥያቄ መመለስ
ነው፡፡ ምክኒያቱም ፈቃዱን ለማድረግ የሚወድ ሰው ካለ እግዚአብሔር ሲናገር ይሰማዋል ይረዳውማል፡፡
ፈቃዱን
ሊያደርግ የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር ቢሆን ወይም እኔ ከራሴ የምናገር ብሆን ያውቃል።የዮሐንስ ወንጌል
7፡17
ፈቃዱን
ለማድረግ የሚወድ ቢኖር ድምፁ ከእግዚአብሔር ይሁን አይሁን ያውቃል፡፡ እግዚአብሔርን የምንሰማው ከሰሚው ችሎታ ሳይሆን ከተናጋሪው
ችሎታ የተነሳ ነው፡፡
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
No comments:
Post a Comment