ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሃጢያታችን እንደሞተ እና ከሙታን እንድተነሳ በምናምን እና በምንመሰክር
ሁሉ ውስጥ መለኮታዊ ህይወት በእኛ ውስጥ ይኖራል፡፡
በውስጣችን የሚኖረው መለኮታዊ ህይወት የራሱ አላማ አለው፡፡ በውስጣችን የሚኖረውን የመለኮታዊ
ህይወት መነሳሳት ከተከተልን እግዚአብሔርን ሙሉ ለሙሉ መከተል እንችላለን፡፡
የእኛ ድርሻ በውስጣችን ያለውን መለኮታዊ ህይወት መስማት እና መከተል ብቻ ነው፡፡ የእኛ
ድርሻ ለራሳችን አላማ እና ፈቃድ መሰቀል መሞት ነው፡፡
በውስጣችን ያለው መለኮታዊ
ህይወት አንድን ነገር ለማሰብ ከተነሳሳ አብረን እናስባለን፡፡
በውስጣችን ያለው መለኮታዊ
ህይወት መሄድ ከፈለገ እግር እንሆንለታለን፡፡
በውስጣችን ያለው መለኮታዊ
ህይወት መናገር ከፈለገ እግር እንሆንለታለን፡፡
በውስጣችን ያለው መለኮታዊ
ህይወት መቀመጥ ከፈለገ እንቀመጣለን፡፡
በውስጣችን ያለው መለኮታዊ
ህይወት መፀለይ ከፈለገ እንፀልያለን፡፡
በውስጣችን ያለው መለኮታዊ
ህይወት መሄድ ከፈለገ እግር እንሆንለታለን፡፡
በውስጣችን ያለው መለኮታዊ
ህይወት አንድን ነገር ለማድረግ ከተነሳሳ አብረን እንሰራለን፡፡
ሃዋርያው ጳውሎስ ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1፡21 ላይ ለእኔ ህይወት ክርስቶስ ነው የሚለው
ስለዚህ ነው፡፡
ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።
በውስጣችን ያለውን መለኮታዊ ህይወት ማመን አለብን፡፡
ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው። ወደ ገላትያ ሰዎች 2፡20
No comments:
Post a Comment