Popular Posts

Friday, June 9, 2023

አስተማሪው ቅባት

 


እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1 የዮሐንስ መልእክት 22027

ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ አዳኛችን በተቀበልን በሁላችን ውስጥ ትልቅ ትንሽ ሳይል በልባችን ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ይኖራል፡፡

መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን የሚኖርበት ዋነኛው ምክኒያት እንዴት የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንደምንፈፅም ሊያስተምረን ሊመራን ነው፡፡

ይህ ዘወትር በውስጣችን የሚኖረው ቅባት ስለሁሉ ያስተምረናል፡፡ ብዙ ጊዜ ስለዋና ነገር እንጂ ስለሁሉ እንደሚመራ ስለማንረዳ ምሪቱን አንጠብቀውም፡፡ በውስጣችን ያለው ቅባት ግን ስለሁሉ ያስተምረናል፡፡

በውስጣችን የሚኖረው የቅባት ምሪት ደረጃውን የጠበቀ የእግዚአብሔር ምሪት ነው፡፡

በውስጣችን ያለው ቅባት ከማንኛውም ነቢይ በላይ አስተማማኝ እውነተኛ ምሪት ነው፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ እንዳስተማራችሁ በእርሱ ኑሩ ይለናል፡፡  

እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2፡20፣27

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa

No comments:

Post a Comment