Popular Posts

Monday, June 12, 2023

የውስጥ ድምፅ

 

እግዚአብሔር ሁልጊዜ ሊመራን ይፈልጋል፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር በመንፈሱ አማካኝነት ከሚመራን መነግዲች ሶስቱ  የውስጥ ምስክርነት ፣ የውስጥ ድምፅ እና የመንፈስ ቅዱስ ድምፅ ይባላሉ፡፡

ከእነዚህ ከሶስት አይነት ድምፆች መካከል እግዚአብሔር አብዛኛውን ጊዜ ሊመራን የሚፈልገው በውስጥ ምስክርነት ነው፡፡ የውስጥ ምስክርነት ሁልጊዜ በውስጣችን የሚኖር እኛ ራሳችን ጊዜ ወስደን በውስጣችን ከፈለግነው የምናገኘው የምሪት አይነት ነው፡፡ የውስጥ ምስክርነት ምልክት እንጂ እግዚአብሔር በድምፅ እንደሚናገረን የሚመጣልን ነገር ድምፅ አይደለም፡፡ 

ይህ የውስጥ ድምፅ እንደ ውስጥ ምስክርነት ሁልጊዜ በውስጣችን የሚኖር ወይም እራሳችን ፈልገን የምናገኘው የምሪት አይነት አይደለም፡፡

የውስጥ ድምፅ መንፈስ ቅዱስ እንደወደደ የሚሰጠን የምሪት ድምፅ ነው፡፡ የውስጥ ምስክርነት ስለአንድ ነገር ስናስብ የሚሰጠን "ነው" ወይም "አይደለም" የሚል የማረጋገጫ ምልክት ነው፡፡ የውስጥ ድምፅ ግን መልእክት ቃል ወይም አረፍተ ነገር ሊሆን ይችላል፡፡

አዎን፥ ሙታንን በሚያነሣ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን፥ እኛ ራሳችን የሞትን ፍርድ በውስጣችን ሰምተን ነበር። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1፡9

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa


No comments:

Post a Comment