በምድር ላይ ብዙ ድምፆች አሉ፡፡ በምድር ላይ
የአእምሮዋችን ሃሳብ አለ፡፡ ሰይጣን በአእምሮዋችን ሃሳብ ሊጠቀም እና ሊያሳስተን ይችላል፡፡ በምድር ላይ ያሉ ድምፆች ሁሉ መሰማት
ይፈልጋሉ፡፡ ታዲያ ከድምፆች መካከል የእግዚአብሔርን ድምፅ ለመስማት የመንፈስን ድምፅ በምናችን እንደምንሰማ ማወቅ አለብን፡፡
የእግዚአብሔርን ድምፅ የምንሰማው በልባችን ነው
እንጂ በአእምሮዋችን አይደለም፡፡ በስጋችን ከስጋዊው አለም ጋር እንገናኛለን በአእምሮዋችን ከእውቀት አለም ጋር እንገናኛለን፡፡
በመንፈሳችን ደግሞ ከመንፈሳዊው አለም ጋር እንገናኛለን፡፡ ታዲያ እግዚአብሔርን ለመስማት አእምሮዋችን በቂ አይደለም፡፡ አእምሮዋችን
እኛ በምናውቀው እውቀት ላይ ብቻ የተወሰነ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን መንፈስ የምንሰማው በመንፈሳችን ነው፡፡ የእግዚአብሔርን መንፈስ
የምንሰማው በአእምሮዋችን ሳይሆን በልባችን ነው፡፡
መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው። በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም። እኛ ግን ከእግዚአብሔር እንዲያው የተሰጠንን እናውቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበልንም። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 2፡11-12
አቢይ
ዋቁማ ዲንሳ AbiY Wakuma Dinsa
No comments:
Post a Comment