Popular Posts

Tuesday, June 6, 2023

የሚመራን የእግዚአብሔር መንፈስ

 


ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ አዳኛችን የተቀበልን ሁላችን የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ ውስጥ ይኖራል፡፡

ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6፡19-20

ሃጢያታችን ይቅር የተባለልን ሁላችን የእግዚአብሔር መንፈስ የሚኖርብን የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ሆነናል፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ይመራናል፡፡

ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ። የዮሐንስ ወንጌል 14፡14-16

ይህ በውስጣችን የሚኖረው መንፈስ የእውነት መንፈስ ነው፡፡ ይህ መንፈስ በሁሉም የህይወታችን ዘርፍ ወደ እውነት ሁሉ ይመራናል፡፡ በውስጣችን ያለውቅባት ስለሁሉ ያስተምረናል፡፡

እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ። እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ። 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 2፡20፣27

አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa


No comments:

Post a Comment