Popular Posts

Tuesday, August 9, 2016

መልካም ምግባር አይበቃም!

መል ካምን መ ስራት መስራት መልካም ነው፡፡ ነገር ግን ለመዳን መልካም ስራ መስራት አይበቃል፡፡ ሰው ከአንዱ ሰርቆ ለሌላው ምፅዋት ቢሰጥ ያደረገው መልካም ስራ ያደረገውን ክፉ ስራ አይሽረውም፡፡ የሰው ችግር በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር መለየቱና መጣላቱ ነው፡፡ 
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ ሮሜ 3፡23 
የዚህ የእግዚአብሄር ክብር የጎደለው ሰው መጨረሻ ለዘላለም ከእግዚአብሄ መለያየት ነው፡፡
የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ ሮሜ 6፡23 ይህንን ለዘላለም ከእግዚአብሄር በመለየት በሞት የሚያስፈርደውን ፍርድ ሊለውጥ የሚችል ማንም ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር ግን በምህረቱ ሃጢያት ያልሰራውን አንድ ልጁን በመስቀል ላይ እንዲሞት በማድርግ የሃጢያታችንን ዋጋ ከፈለ፡፡ 
አሁን ሰው እግዚአብሄር ያዘጋጀውንም ይህንን የመዳኛ መንገድ እየሱስን ከተቀበለና እየሱስ ከሙታን እንደተነሳ በልቡ ካመነ እንዲሁም እየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፉ ከመሰከረ ይድናል፡፡ 
ኢየሱስ ጌታ እንደ ሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህና፤ ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና። ሮሜ 10፡9-10 
ምንም በሰራው መልካም ስራ ሳይሆን እግዚአብሄር ለመዳኛ የሚሆነውን የሃጢያትን እዳ የከፈለውን እየሱስን የተቀበለውን እግዚአብሄር ልጅ አድርጎ ይቀበለዋል፡፡ 
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ዮሃንስ 1፡12 
በመልካም ስራው ሳይሆን እየሱስን በማመን ብቻ የዳነው ሰው እግዚአብሄር ያዘጋጀለትን መልካመ ስራ በመስራት እግዚአብሄርን ያስደስተዋል፡፡ 
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ 
 

No comments:

Post a Comment