Popular Posts

Wednesday, August 10, 2016

ከዋናተኛው ሮቤል ምን እንማራለን ?




ዛሬ ኢትዮጲያን ወክሎ ስልተወዳደረ ዋናተኛ ብዙ ተብሎዋል፡፡ ይህን አስቂኝ ዜና ዴይሊ ሜይል እስከ ዋሽንግተን ፖስት በግርምታ ዘግበውታል፡፡

ይህንን ዜና የስፖርትና ሌሎችም ጋዜጠኞች በፌስቡክና በትዊተር ገፆቻቸው ተችተውበታል፡፡ በርግጥ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኖዋል፡፡ ሁኔታው ያስቃልም ያስቆጫልም፡፡ እያንዳንዳችን ግን ከዚህ ምን እንማራለን የሚለው መጠየቅና ከስህተት መማር ብልህነት ነው፡፡

ምክኒያቱም ይህ ክስተት በዚህ በ24 ዓመት ወጣት ላይ ወደቀበት እንጂ ይህ ክስተት ከዚህ ያለፈ ነው፡፡ ወጣቱ ለየት ያለ ነገር መስራት እፈልጋለሁ ብሎ ነው የሄደው ከዚያም በውጤቴ ደስተኛ ነኝ ብሏል፡፡

ከእርሱ በላይ ስልጣን ያላቸው መሪዎች ልከውታል ፡፡ ለዚህም ውሳኔያቸው ሃላፊነቱንም መውሰድ ያለባቸው መሪዎቹ ናቸው፡፡ ይህ ሁኔታ ግን በዚህ በዋና ፌዴሬሽኑ አይወሰንም፡፡ ሌሎችም ፌዴሬሽኖች በዚህ አጋጣሚ ራሳቸውን ሊያዩ ይገባል፡፡

በአጠቃላይ መንግስትም በየደረጃው ያሉ የአመራር አካላት ራሳቸውን ከአድሎ እንዲጠብቁ  ትትልና አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ ሊወስድ ይገባል፡፡ መንግስት በየደረጃው ያሉ የመንግስት ባለስልጣናት ተመሳሳይ ነገር እንዳያደርጉ ስልቶችን መፍጠርና መድሎንና ሙስናን መከላከል እንዳለበት ራሱን የሚያይበት መልካም አጋጣሚ ነው፡፡

ይህ በአለም መድረክ የተደረገው ነገር በየመስሪያ ቤቱ እንዳይደረግ በየደረጃው ያሉ የመንግስት ባለስልጣኖች ወደራሳቸው የሚያዩበትና አሰራራቸውን የሚፈትሹበት እንዲሁም አድሎን ለመዋጋት በትጋት ለመስራት የሚወስኑበት መልካም አጋጣሚ ነው፡፡

ግልፅነትና ተጠያቂነት በአግባቡ ካልሰፈነ እንደዚህ የሚያዋርድ ነገር ይከሰታል፡፡ ከዚህም በላይ አድሎ የሚደረግባቸውን ሰዎች ልብ ያሳዝናል፡፡

መንግስት ብቻ ሳይሆን እኛም እያንዳንዳችን ባለንበት ስልጣንና የመሪነት ደረጃ ይህን አይነት ስህተት ላለመስራት ወደ ራሳችን ማየት ይኖርብናል፡፡ በጓዳ የምንሰራው በደል በአደባባይ ሊያጋልጠን እንደሚችል ማሰብ አለብን፡፡

ይገርማል ብለን ስቀንና ተቆጭተን ብቻ ብናልፍና እያንዳንዱ የህይወት ክፍላችንን ለመፈተሽ ይህን አጋጣሚ ካልተጠቀምንበት እና በእውነት ለመኖር ካልወሰንን ይህን አጋጣሚ በከንቱ እናባክነዋለን፡፡

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ 

No comments:

Post a Comment