Popular Posts

Follow by Email

Tuesday, August 23, 2016

ለሚጠሩት ባለጠጋ ነው

በአለም ላይ የሃብት ችግር የለም፡፡ በአለም ላይ ለሁሉም ሰው የሚበቃ ምንጭ አለ፡፡ እግዚአብሄር የአቅርቦች ችግር የለበትም፡፡ እግዚአብሄር ባለጠጋ ነው፡፡ በአለም ላይ ያለው ችግር እግዚአብሄርን ያለመፈለግና እግዚአብሄርን ያለመጥራት ችግር ነው፡፡ በምድር ላይ ያለው ችግር ወደ እግዚአብሄር ያለመፀለይ ችግር ነው፡፡
እግዚአብሄር ባለጠጋ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ባለጠግነት የሚጠቀሙበት የሚጠሩት ናቸው፡፡ የሚጠሩት የእግዚአብሄር ባለጠግነት ተካፋዮች ይሆናሉ፡፡ የሚጠሩት በእግዚአብሄር ባለጠግነት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
ከባለጠግነቱ ተካፋዮች የሚሆኑት ሃብታሞች ብቻ አይደሉም ፡፡ ከእግዚአብሄር ባለጠግነት የሚጠቀሙት የሚሆኑት ሃያላን ብቻ አይደሉም፡፡ ወይም ደግሞ ከእግዚአብሄር ባለጠግነት የሚካፈሉት ጠቢባብን ብቻ አይደሉም፡፡ የሚጠሩት ሁሉ ከባለጠግነቱ ተካፋይ ይሆናሉ፡፡ ለሚጠሩት ሁሉ ባለጠጋ ነው፡፡
በአይሁዳዊና በግሪክ ሰው መካከል ልዩነት የለምና፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ ለሚጠሩትም ሁሉ ባለ ጠጋ ነው፤ ሮሜ 10፡12
እግዚአብሄርን ያየው አንድስ እንኳን የለም በእቅፉ ያለው አንድ ልጁ ተረከው የተባለለት እየሱስ ስለእግዚአብሄር ልብ ሲተርክ እንዲህ ይላል፡፡
ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። ማቴዎስ 7፡7
ለምኑ እንጂ ያለው በንግዳችሁ ልክ ለምኑ አላለም፡፡ ፈልጉ እንጂ ያለው በደሞዛችሁ ልክ ፍለጋችሁን ወስኑት አላለም፡፡ አንኳኩ እንጂ ባላችሁ ካፒታል ልክ አንኳኩ አአላለም፡፡
የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል። ማቴዎስ 7፡8
የእግዚአብሄር ባለጠግነት ከሃብቱ እንድትጠቀሙ ለእናንተ ነው፡፡ ልመናችሁን በገቢያችሁ አትወስኑት ፡፡ ፀሎታችሁን በሃብታችሁ አትወስኑት፡፡ እግዚአብሄርን በኑሮዋችሁ ደረጃ አትወስኑት፡፡
እግዚአብሄርን ካልጠራነው ግን የባለጠግነቱ ተካፋይ ልንሆን አንችልም፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
#ለምኑ #ባለጠግነት #አንኳኩ #ሃብት #እምነት #ፀሎት #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment