Popular Posts

Follow by Email

Thursday, August 4, 2016

የፍቅር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱእግዚአብሄር የፍቅር አምላክ ነው፡፡ ሰውን ወዶና ፈቅዶ የፈጠረው እግዚአብሄር ነው፡፡ እግዚአብሄር ሰዎችን ይወዳል፡፡ እግዚአብሄር ወዳጅ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሄር ራሱ ፍቅር ነው፡፡
 
ስለፍቅር ትርጉም ማንኛውም ክርክር ቢነሳ ማጣቀሻ ሊሆን የሚችለው እግዚአብሄር ነው፡፡ የፍቅር ትርጉሙን የምናገኘው ከእግዚአብሄር ነው፡፡
 
እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል፤ 1 ዮሃንስ 316

የእግዚአብሄር ፍቅር ደግሞ ለሁላችንም ለሁልጊዜያችን ለሁሉም ነገራችን በቂ ነው፡፡ ስለዚህ ነው እየሱስ በፍቅሬ ኑሩ ያለው፡፡
በፍቅሬ ኑሩ ሲል በፍቅሬ ብሉ በፍቅሬ ጠጡ በፍቅሬ ውጡ በፍቅሬ ግቡ በፍቅሬ ተመላለሱ በፍቅሬ ተጠበቁ በፍቅሬ አሸንፉ በፍቅሬ ተከናወኑ በፍቅሬ ብዙ በፍቅሬ አፍሩ በፍቅሬ እረፉ እያለ ነው፡፡
 
የእግዚአብሄር ፍቅር መጨረሻ እንደሌለው ውቂያኖስ  ነው፡፡
 
የገንዳ ውሃ ዋናተኛ እንደልቡ ዘሎ ጠልቆ ዳይቭ አይገባበትም፡፡ የገንዳ ውሃ ዋናተኛ እንደፈለገ ወደፊት በፍጥነት አይዋኝም ግድግዳው ይመታኛል ብሎ ይፈራል፡፡ የገንዳ ዋና የውሃው ትንሽነትና ውስንነት ዋናተኛውን ውስን ያደርገዋል፡፡
 
የእግዚአብሄር ፍቅር ግን ካለምንም ፍርሃት እንድኖር የሚያስችል በቂ ከውቂያኖስ የሰፋ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር በእረፍት የምንሮርበት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር በነፃነት የተሞላ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር  በአቅርቦት የተሞላ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር በሰላም የተጥለቀለቀ ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር እረፍት የሞላበት ነው፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር እርካታ የማይጎልበት ነው፡፡

የእግዚአብሄር ፍቅር ውስን አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር የምንፈራበት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር የምንሳቀቅበት አይደለም፡፡ የእግዚአብሄር ፍቅር የምንወሰንበት አይደለም፡፡
 
የእግዚአብሄር ፍቅር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ከመታወቅ የሚያልፍ ነው፡፡
 
ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ ኤፌሶን 3:18-19

ይህንን ፍቅር ግን የምንረዳው በቤተሰብ ውስጥ ነው፡፡ ይህን ፍቅር የምንረዳው ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ነው፡፡ 

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ 


#ፍቅር #የእግዚአብሄርፍቅር #የክርስቶስፍቅር #አማርኛ #ኢትዮጲያ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ  #አቢይዋቁማዲንሳ 

No comments:

Post a Comment