Popular Posts

Monday, August 1, 2016

ሕይወታችሁ ምንድር ነው?



በአለም ላይ ያለው ነገር ሁሉ አላፊ ጠፊም ነው፡፡ የሚታየው ነገር ሁሉ ያልፋል፡፡ ሁሉም ነገር ያልፋል፡፡ ምክኒያቱም የሚታየው ነገር ሁሉ ከማይታየው ነው የመጣው፡፡ 

ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን። ዕብራውያን 11፡3

አሁን በአይን የሚታየው ነገር ሁሉ ሃላፊ ነው ፡፡ መንፈሳዊው አለም በአይን የማይታየው አለም ብቻ ነው ቋሚና የማያልፈው፡፡  

የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 4፡18

የሰውን ህይወት እንኳን ስንመለከት ከዘላለም ጋር ሲነፃፀር ህይወቱ ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ነው፡፡
ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና። ያዕቆብ 4፡14

ስለዚህ ነው መፅሃፍ ቅዱስ በላይ ያለውን እሹ የሚለው፡፡ በላይ ያለው መንፈሳዊው አለም ዘላቂውና ቋሚው አለም ብቻ ነው አስተማማኝ ፡፡ እርሱ ብቻ ነው የማያልፈው፡፡ 

እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ እሹ፤ በላይ ያለውን አስቡ እንጂ በምድር ያለውን አይደለም። ቆላስይስ 3፡1-2

ለዘላለም የሚኖረው ሰማዩንና ምድሩን የፈጠረው የእግዚአብሄር ቃል ነው፡፡ እንዲሁም የእግዚአብሄርን ቃል የሚያደርግ ሰው ለዘላለም ይኖራል፡፡ 

ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል። 1ኛ ዮሐንስ 2፡17

ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ 


#ኢየሱስ #ጌታ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #እንፍዋለት  #ሕይወታችሁ #ዘላለም #የእግዚአብሄርቃል  #የእግዚአብሔርፈቃድ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment