Popular Posts

Monday, August 15, 2016

በድካሜ እመካለሁ

ክርስትና አስደናቂና አስገራሚ ጉዞ ነው፡፡ እግዚአብሄር ወደ መንግስቲቱ ሲጠራን የጠራን በራሱ ሃይል ተማምኖ ነው፡፡ ክርስትናንም ከሌሎች ሃይማኖቶች ልዩ የሚያደርገው በእግዚአብሄር ሃይል የምንኖረው ኑሮ ስለሆነ ነው፡፡
አንተም ዛሬ ሃይል እንዳጠረህ ተሰምቶህ ይሆን ፡፡ ለደከመህ ላንተ የምስራች አለኝ፡፡ የእግዚአብሄርን እርዳታ የምታገኝበት ትክክለኛ ጊዜ ላይ ደርሰሃል፡፡ እንዲያውም ነገሮችን በራስህ ለማድረግ እንደምትችል እስካሁን እያሰብክ ከሆነ ተጠንቀቅ፡፡
በስጋህ ሃይል በሰው ክንድ ተስፋ ካልቆረጥክ በተሳሳተ መንገድ ላይ ነህ፡፡ ነገር ግን በራስህ ሃይል ተስፋ ስትቆርጥና የእግዚአብሄርን እርዳታ በሙሉ ልብህ ስትፈልግ የእግዚአብሄር ሃይል እንዲያድርብህ መንገድ ይከፍታል በእግዚአብሄርም ጉልበት ትበረታለህ፡፡
እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና። 2ኛ ቆሮንቶስ ሰዎች 12፡9-10
ስለዚህ ነው በክርስትና ሁል ማሸነፍ ያለው፡፡ በድካማችንም እንኳን ደስ ይለናል ምክኒያቱም የእግዚአብሄር ሃይል ስለሚያድርብን እኛው ነን አሸናፊዎቹ፡፡
ስንደክም የእግዚአብሄር ሃይል በእኛ በሃይል ስለሚሰራ እንበረታለን፡፡ ሐዋሩያው ጳውሎስ እንዲያውም ስደክም የእግዚአብሄር ሃይል በእኔ ስለሚያድር በድካሜ እመካለሁ ይለናል፡፡
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር share ማድረግ ቢወዱ
#የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #መመካት #ብርታት #እምነት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment