Popular Posts

Follow by Email

Wednesday, August 10, 2016

አዋጅ !

እግዚአብሄር ፈጥሮናል፡፡ እግዚአብሄር የፈጠረን ለእርሱ ነው፡፡ ይህ ጥሪ ዘር ሃይማኖት ፆታ ሳይለይ ለሁሉም የቀረበ ጥሪ ነው፡፡ የትኛውም ዘር የትኛውም ሃይማኖት የትኛውም ፆታ አየመለከተኝም የሚል የለም፡፡ ሁሉንም ይመለከታል፡፡ ከሁሉም አፋጣኝ ውሳኔ ይጠይቃል፡፡ ይህ ለራሱ ክብር የፈጠረን አምላክ ለሁላችንም እንዲህ ይላል፡፡ ለሁላችንም እንዲህ ይለናል፡፡
ለሁሉም እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ዕለት ዕለት ተሸክሞ ይከተለኝ። ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠፋታልና፤ ስለ እኔ ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን እርሱ ያድናታል። ሉቃስ 9፡23-24
እኛን የፈጠረው አምላክ ከእኛ ሙሉ መታዘዘን ይጠይቃል፡፡ እርሱን እንዳንከተል ሊበቃ የሚችል ምንም ምክኒያት የለም፡፡ ጌታን እንዳንከተል የሚቀርብ ማንኛውም ምክኒያት ሰንካላ ምክኒያት ነው፡፡ ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም። ሉቃስ 14፡27
ጌታን የምንከተለው ለራሳችን ነው፡፡ ጌታን የምንከተለው እንዳንጠፋ ነው፡፡ ጌታን የምንከተለው ለዘላለም ከጌታ እንዳንለያይ ነው፡፡ ጌታን የምንከተለው የእግዚአብሄር ቁጣ በእኛ ላይ እንዳይኖር ነው፡፡ እግዚአብሄር እንደሆነ ኩሩ ነው፡፡
እግዚአብሄር ከፈጠረው ሰው ያነሰ ነገር አይቀበልም፡፡ እግዚአብሄር ከእኛ ሙሉ መሰጠትን ይጠይቃል፡፡ ለዚህ ነው ራሱን የማይክድ ሰው ለእኔ ሊሆን አይገባውም የሚለው፡፡
አንዱ አስቀድሜ አባቴን ልቅበር ባለው ጊዜ እየሱስ አይ ችግር የለም ጊዜ አለህ ቀስ ብለህ ትከተለኛለህ አላለውም፡፡ ጌታን የመከተያ ጊዜው አሁን ነው፡፡ ሌላውንም፦ ተከተለኝ አለው። እርሱ ግን፦ ጌታ ሆይ፥ አስቀድሜ ልሂድና አባቴን እቀብር ዘንድ ፍቀድልኝ አለ።
ኢየሱስም፦ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤ አንተስ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስበክ አለው። ሉቃስ 9፡59-60
አንዱ እከተልሃለሁ ነገር ግን ቀድሜ ቤተሰቦቼን ልሰናበት ባለው ጊዜ የተከፋፈለ መሰጠትና ትኩረት ተቀባይነት እንደሌለው ነው እዚያው ያስረዳው፡፡
ደግሞ ሌላው፦ ጌታ ሆይ፥ እከተልሃለሁ፤ ነገር ግን አስቀድሜ ከቤቴ ሰዎች እንድሰናበት ፍቀድልኝ አለ። ኢየሱስ ግን፦ ማንም ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም አለው። ሉቃስ 9፡61-62
ይህንን ፅሁፍ ሼር ማድረግ ቢወዱ
#ወንጌል #ደቀመዝሙር #ኢየሱስ #ጌታ #መዳን #አማርኛ #ኢትዮጲያ #አቢይዋቁማ #ፌስቡክ #አዋጅ

No comments:

Post a Comment