Popular Posts

Thursday, October 11, 2018

እግዚአብሄር ብቻ ሊሞላው የሚችለው ክፍት ቦታ


ሰው የተፈጠረው ለእግዚአብሄር ክብር ነው፡፡ ሰው የተፈጠረው ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት እያደረገ እንዲኖው ነው፡፡
የመጀመሪያው ሰው አዳም እግዚአብሄርን ባለመታዝዝ ከእግዚአብሄር ተለየ፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ሲለይ ከህይወቱ ተለየ፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ሲለይ ከአላማው ተለየ፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ሲለይ ከክብሩ ተለየ፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ሲለይ ከህይወት ትርጉሙ ተለየ፡፡
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 3፡23
ሰው የተፈጠረው ከእግዚአብሄር ተለይቶ እንዲኖር ባለመሆኑ ሰው ከእግዚአብሄር ሲለይ በህይወቱ ትልቅ ከፍተት ተፈጠረ፡፡
አሁን በምድር ላይ የምታዩት ረብሻ ሁሉ ሰው ያንን እግዚአብሄር ብቻ ሊሞላው የሚችለውን ክፍተት በተለያየ ነገር ለመሙላት በሚያደርገው ጥረት የሚፈጠር ረብሻ ነው፡፡
ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም። የዮሐንስ ወንጌል 14፡27
ሰው እግዚአብሄር ብቻ ሊሞላው የሚችለውን ክፍተት በዝና ሊሞላው ሲሞክር ዝናውን ባገኘው መጠን እየጠላው ይሄዳል፡፡ ሰው በእግዚአብሄር ብቻ ሊሞላ የሚችለውን የህይወቱን ክፍተት ለመሙላት ብዙ ገንዘብ እንደሚያስፈልገው ሲያስብ ገንዘቡን ለማግኘት ሰውን እያጣ ያሄዳል፡፡ ሰው እግዚአብሄር ብቻ የሚሞላውን የህይወቱን ክፍተት ለመሙላት ደስታ ይሰጠኛል የሚለውን ስካርን አደንዛዠ እፅ እና ዝሙትን ይከተላል፡፡
ሰው ምንም ቢለፋና ቢጥር እግዚአብሄር ብቻ በህይወቱ ያለውን ክፍተት ሊሞላ የሚችለው ምንም ነገር አያገኝም፡፡ ሰው በህይወቱ ያለው ክፍተት እንፈዲሞላ ከክፉ መንገዱ በመመለስ ንስሃ መግባት ይገባዋል፡፡ ሰው የህይወቱ ክፍተት እንዲሞላ እግዚአብሄር ያዘጋጀለትን የመዳኛ መንገድ ኢየሱስን መቀበል ይገባዋል፡፡
ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ የዮሐንስ ወንጌል 1፡12
ሰው የህይወቱን ክፍተት ለመሙላት እንደገና የእግዚአብሄር ልጅ በመሆን እግዚአብሄርን ሊያመልክ ይገባዋል፡፡
እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል። 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2፡25
አሁን ኢየሱስን ለመቀበል ከወሰንክ ይህንን ፀሎት ከልብህ ወደ እግዚአብሔር ፀልይ
እግዚአብሄር ሆይ የመዳንን እውቀት ስለላክልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ሃጢያተኛ እንደሆንኩ አውቃለሁ፡፡ በሃጢያቴ ካንተ እንደተለሁ አውቃለሁ፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያቴ በመስቀል ላይ በመሞት የሃጢያቴን ዋጋ ሁሉ እንደከፈለ አውቄያለሁ፡፡ ኢየሱስ በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው፡፡ ልጅህ አድርገህ ወደ ቤተሰብህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት #ጸጋ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment