Popular Posts

Friday, October 12, 2018

እግዚአብሄር ጀማሪ ነው


እግዚአብሄር በማንም አይመራም፡፡ እግዚአብሄርን ማንም አያስታውሰውም፡፡ እግዚአብሄርን ማንም አያማክረውም፡፡
እግዚአበሄር የሚሰራውን ያውቃል፡፡ እግዚአብሄር ስለሚሆነው ነገር ሙሉ እውቀት አለው፡፡ እግዚአብሄር ነገር ከየት ጀምሮ የት እንደሚጨርስ መጀመሪያውንና መጨረሻውን ያውቃል፡
እኔ አምላክ ነኝና፥ ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም። በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ እላለሁ። ትንቢተ ኢሳይያስ 46፡9-10
እግዚአብሄር ምድርንና ሰማይን ከመፍጠሩ በፊት ምድርና ሰማይን ለመፍጠር ፈለገ ፣ አቀደና ፈጠረ፡፡
እግዚአብሄር ሰውን ከመፍጠሩ በፊት እንደ ሰው አይነት ፣ ሰው እንደሚሰራው አይነትን ስራ የሚሰራ ፍጡር መፍጠር ፈለገ፡፡ እግዚአብሄር ሰውን በመልኩና በአምሳሉ ፈጠረ፡፡
ሰው አግዚአብሄር አታድርግ ያለውን በማድረግ ሰው ከእርሱ ከተለያየ በኋላ እግዚአብሄር ህዝብ ይሆነው ዘንድ አብርሃም መረጠና ጠራው፡፡
እግዚአብሄር ከአብርሃም ከይስሃቅና ከያቆብ ዘር የእስራኤልን ህዝብ ለራሱ መረጠ፡፡ እግዚአብሄር የእስራኤልን ህዝብ ከግብፅ ምድር በማውጣት ለራሱ የተለየ ህዝብን አደረገ፡፡  
እግዚአብሄር ያቀደው ጊዜ በደረሰ ጊዜ በእስራኤል ህዝብ በኩል አህዛብ ሁሉ የሚባረኩበትን ኢየሱስን አመጣ፡፡
 ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ ወደ ገላትያ ሰዎች 4፡4
እግዚአብሄር ኢየሱስን ለተቀበሉ ሰዎች ሁሉ ለእያንዳንዳቸው የተለየ የህይወት እቅድ አለው፡፡ እግዚአብሄር ለልጆቹ ማንም እቅድ እንዲያቀብለው አይጠብቅም፡፡ እግዚአብሄር ጀማሪ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ምን እንደሚያደርግ ያውቃል፡፡ ከመፈጠራችን በፊት የምንሰራው ነገር ተዘጃግጅቶ አልቆ ነበር፡፡ የተፈጠርንውም የምንሰራው ነገር ስለነበር ነው፡፡
እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡10
እግዚአብሄር ለህይወታችን ያለውን እቅድ በትጋት እየሰራበት ነው፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው አንድ ነገር እግዚአብሄር ባወጣው እቅድ ውስጥ መግባት ለመግባት የእግዚአብሄርን ፊት መፈለግ ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሄር የሚለውን መከተልና ማድረግ ለሰው በቂ ነው፡፡  
እግዚአብሄር በህይወታችን ያለውን አላማ ለመፈፀም ለነገሮች ልባችንን ያነሳሳል፡፡ እግዚአብሄር በህይወታችን ያቀደው የህይወት አላማ መፈፀሚያው ጊዜ ሲደርስ እኛ እንኳን የረሳነውን ነገር እንደገና ይቆሰቁሳል ልባችንን ያነሳሳል፡፡ ሰው ረስቶታል ብሎ እግዚአብሄር የሚተወው ነገር የለም፡፡ እግዚአብሄር አላማው እስኪፈፅም አያርፍም፡፡  
እግዚአብሄር ፈጣሪ ነው፡፡ እግዚአብሄር ጀማሪ አምላክ ነው፡፡ እግዚአብሄር ፈር ቀዳጅ ነው፡፡ እግዚአብሄር ግድ የሚለው ባለቤት ነው፡፡ መልካምን ነገር በማሰብ እግዚአብሄርን ማንም አይቀድመውም፡፡
ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ አውቃለሁ፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይደለም። ትንቢተ ኤርምያስ 29፡11
እግዚአብሄር በህይወታችን ያለውን አላማ ሊፈፅም በዝምታም ይሁን በዝግታ በመስራት ይተጋል፡፡ እኛ ስንተኛ ሁሉ እግዚአብሄር በትጋት በስራ ላይ ነው፡፡
ስለዚህ ነው እረፉ እኔም አምላክ እንደሆንኩ እወቁ የሚለው፡፡
እረፉ እኔም አምላክ እንደሆንኩ ዕወቁ፡፡ መዝሙረ ዳዊት 46:10
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር   share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes

#የእግዚአብሄርምክር #የእግዚአብሔርፈቃድ #እግዚአብሔር #ህብረት #እምነት #የሰውአሳብ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment