Popular Posts

Wednesday, October 3, 2018

ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም


ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡8-9
ደህንነት ነፃ ስጦታ ነው፡፡ ሰው በሃጢያቱ ምክኒያት በእግዚአብሄር ላይ ካመፀ በኋላ ከእግዚአብሄር ተለያይቷል፡፡ በእግዚአብሄር ክብር የተፈጠረው ሰው በሃጢያቱ ምክኒያት ከእግዚአብሄር ክብር ወድቆዋል፡፡
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ ወደ ሮሜ ሰዎች 3፡23
እግዚአብሄር ሰውን ለዘላለም ጥፋት ስላልፈጠረው ራሱ የመዳኛ መንገድ አዘጋጅቶለታል፡፡ ሰው እግዚአብሄር በክርስቶስ ያዘጋጀውን የመዳኛ መንገድ ከተቀበለ ከጥፋት ይድናል፡፡ በሃጢያቱ ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር ጠላት የሆነው ሰው በክርስቶስ ኦየሱስ የተከፈለለትን የሃጢያት እዳ ክፍያ ለእኔ ነው ብሎ ከተቀበለ ከእግዚአብሄር ጋር ይታረቃል፡፡
ሰው የሚድነው ይህን የፀጋ ስጦታ ሲቀበል ነው፡፡ ሰው የሚድነው ኢየሱስ እንደአዳኙ ሲቀበል ብቻ ነው፡፡
ሰው በሃጢያቱ ሙት ስለሆነ ሰው የሚድነው በመልካም ስራ አይደለም፡፡ በሃጢያቱ ፍፁም ከእግዚአብሄር የተለያየው ሰው የቱንም ህግ በመጠበቅ ሊድን አይችልም፡፡ ሃጢያተኛው ስው በቅዱሱ በእግዚአብሄር ፊት በመልካም ባህሪ ሊድን አይችልም፡፡ የሃጢያተኛው ሰው ፅድቅ በእግዚአብሄር ዘንድ አፀያፊ ነው፡፡
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል። ትንቢተ ኢሳይያስ 64፡6
ሰው የሚድነው ኢየሱስ በመስቀል ላይ የከፈለለትን የሃጢያት ዋጋ ለእኔ ነው ብሎ በእምነት ሲቀበል ብቻ ነው፡፡
ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡8-9
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት #ጸጋ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment