Popular Posts

Wednesday, October 10, 2018

ከመጠን በላይ የምንጓጓው ስለማናውቀው ነው


ሰው የአንድን ነገር ጥቅም ብቻ ሲያውቅ ያንን ነገር ለማግኘት በጣም ይጓጓል፡፡ በህይወታችን በጣም የምንጓጓለት ምንም ነገር ቢኖር እንረጋጋ፡፡ በህይወታችን በጣም የምንጓጓለት ምንም ነገር ቢኖር መጀመሪያ ይህ እንደዚህ የምጓጓለትን ነገር ሃላፊነትቱ በትክክል አውቀዋለሁ? ብለን ራሳችንን እንጠይቅ፡፡
በጣም የምጓጓለትን ነገር ሃላፊነቱን እስከምናውቅ ድረስ ማግኘታችን አደገኛ ነው፡፡ ጥቅሙን ብቻ እንጂ ሌላውን ጎኑን ሃላፊነቱን የማናውቅ ከሆነ አጠቃቀሙን እንደማናውቅ የኤሌክትሪክ ሃይል ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ የሚያመዝን ሊሆንብን ይችላል፡፡ ሃላፊነቱን የማናውቀው ነገር በቀላሉ ያሰናክለናል፡፡
ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥ የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፥ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥ በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7፡29-31
ነገር ሁሉ ጊዜያዊ እንደሆነ አስብ፡፡ ነገ ልታዝን እንደማትችል አድርገህ ዛሬ ደስ አይበልህ፡፡ ነገ ደስታ እንደሌለ አድርገህ ዛሬ አትዘን፡፡
ደስታም የራሱ ሃላፊነት አለው፡፡ ሃዘንም የራሱ ሃላፊነት አለውከሃላፊነት ውጭ የሚመጣ ጥቅም የለም፡፡ እውነተኛ ጥቅም የሚመጣው ከሃላፊነት ጋር ነው፡፡
የተዋረደው ወንድም ግን በከፍታው፥ ባለ ጠጋም በውርደቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ያልፋልና። ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል። የያዕቆብ መልእክት 1፡9-11
ከመጠን በላይ የምንጓጓው ሃላፊነቱን ስለማናውቅ ነው፡፡ ከመጠን በላይ የምንጓጓው ጊዜያዊነቱን ስለማናውቅ ነው፡፡
ሰው የሆነ ነገር ስለማግኘቱ በጣም ሲፈነጥዝ ሲታይ ያስፈራል፡፡ ይህ ሰው ባገኘው ጥቅም እንደዚህ በጣም እንደፈነጠዘ ሁሉ በሃላፊነቱም እንደዚሁ ይሆን ይሆን ብሎ ያሳስባል፡፡
አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን ተቀበል፥ . . . አገልግሎትህን ፈጽም። 2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 4:5
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ይህን ፅሁፍ ለሌሎች ሼር  share ማድረግ ቢወዱ
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ጥበብ #ማስተዋል #መረዳት #ሃያል #ጠቢብ #ባለጠጋ #ውርደቱ #ይመካ #የእግዚአብሄርሃይል #መንፈስቅዱስ #መመካት #ብርታት #እምነት #እወጃ #ቤተክርስትያን #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #መንፈስቅዱስ #ህይወት #ፌስቡክ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ  

No comments:

Post a Comment