Popular Posts

Monday, October 1, 2018

እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም


ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም። የዮሐንስ ወንጌል 14፡27
በአለም እውነተኛ ሰላም የለም፡፡ በአለም ያለው ሰላም ማስመሰያው ሰላም ነው፡፡ በአለም ያለው ሰላም ትክክለኛው ሰላም አይደለም፡ 
ሰው የተፈጠረው በሰላም ነው፡፡ ሰው የሚኖረው በሰላመ ነበር፡፡ ሰው አትብላ የተባለውን በመብላት እግዚአብሄር ላይ ካመፀ በኋላ ሰላሙን አጣው፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ግንኙነት ሲበላሽ ሰላምን አጣ፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ሰላሙን ሲያጣ ከራሱ ጋር ሰላም መሆን አልቻለም፡፡ ሰው በሃጢያት ምክኒያት ከእግዚአብሄር ጋር ሰላሙን ሲያጣ ከሰው ጋር ሰላም መሆን አልቻለም፡፡
በሃጢያት ምክኒያት ሰው ሰላም የለውም፡፡ በሃጢያት ምክኒያት ሰው እውነተኛ ሰላም የለውም፡
ሰው የተፈጠረበትን እውነተኛውን ሰላም ለመተካት ማስመሰያውን ሰላም ይፈልጋል፡፡ ሰው ያለው ሰላም በእግዚአብሄር ሳይሆን በነገሮች ያለ እውነተኛ ያልሆነ ሰላም ነው፡፡ ሰው ያለው ሰላም በገንዘብ እና በቁሳቁስ ላይ የተመሰረተ ሰላም ነው፡፡ ሰው ያለው ሰላም በዝና ላይ የተመሰረተ ሰላም ነው፡፡ ሰው ያለው ሰላም እንደ ጊዜውና ሁኔታው የሚለዋወጥ ጊዜያዊ ሰላም ነው፡፡ ሰው ያለው ሰላም እውነተኛና ዘላቂ ሰላም አይደለም፡፡ ሰው ያለው ሰላም ከውስጥና ከልብ የሆነ ሰላም አይደለም፡፡ ሰው ያለው ሰላም ውጫዊ ሰላም ነው፡፡
ሰው ከፈጠረው ከእግዚአብሄር ጋር ሰላም ሳይሆን ከማንም ጋር ሰላም ለመሆን መፈለግ ሞኝነት ነው፡፡
ሰው ሰላ መመለስ ካለበት ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ሰላም መመለስ አለበት፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ሰላም ካልሆነ ከራሱ ጋር ሰላም አይሆንም፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ሰላም ካልሆነ ከሰዎች ጋር ሰላም አይሆንም፡፡ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ሰላም ካልሆነ ከሁኔታዎች ጋር ሰላም አይሆንም፡፡
ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ጠላት ሆኖ እግዚአብሄር ከፈጠረው ከሌላው ሰው ጋር እውነተኛ ወዳጅነት ሊመሰርት መሆን አይችልም፡፡  
እግዚአብሄር የሰውን ሰላም ለመመለስ በክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ዋጋ ከፍሎዋል፡፡ ማንም ሰው እግዚአብሄር በክርስቶስ የከፈለውን ዋጋ ለእኔ ነው ብሎ ቢቀበል ከእግዚአብሄር ጋር ይታረቃል፡፡ ሰው እግዚአብሄር ያዘጋጀውን የሰላም መንገድ ኢየሱስን ቢቀበል ከእግዚአብሄር ጋር ሰላም ይሆናል፡፡
እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው። መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፡14-17
ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም። የዮሐንስ ወንጌል 14፡27
አሁን ኢየሱስን ለመቀበል ከወሰንክ ይህንን ፀሎት ከልብህ ወደ እግዚአብሔር ፀልይ
እግዚአብሄር ሆይ የመዳንን እውቀት ስለላክልኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ሃጢያተኛ እንደሆንኩ አውቃለሁ፡፡ በሃጢያቴ ካንተ እንደተለሁ አውቃለሁ፡፡ ኢየሱስ ስለሃጢያቴ በመስቀል ላይ በመሞት የሃጢያቴን ዋጋ ሁሉ እንደከፈለ አውቄያለሁ፡፡ ኢየሱስ በሶስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ እንደተነሳ አምናለሁ፡፡ ኢየሱስ ጌታ ነው፡፡ ልጅህ አድርገህ ወደ ቤተሰብህ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ በኢየሱስ ስም፡፡ አሜን፡፡
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #ልጅነት #ደህንነት #ሰላም #መልካምስራ #መልካምምግባር #ሞት #አላማመሳት #ሐጢያት #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #ቃል #ፍጥረት #ልጅነት #ስራ #እምነት #አምባሳደር #ብርሃን #ጨው #ልጅነት #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment