Popular Posts

Saturday, October 6, 2018

የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም


ነገር ግን የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም። ስለዚህ በጨለማ የምትናገሩት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፥ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ የምትናገሩት በሰገነት ላይ ይሰበካል። የሉቃስ ወንጌል 12:2-3
የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፥ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም። የሉቃስ ወንጌል 8:17
ሰዎች የሰውን መልካም ስራ ለመደበቅ ምንም ቢጥሩ የሰው መልካም ስራ አንድ ቀን ወደ ብርሃን ይወጣል፡፡ የሰውን መልካም ስራ እስከ መጨረሻው ደብቆ ሊያጠፋው የሚችል ሰው የለም፡፡ ሰዎች ክፋታቸውን ሊደብቁ ምንም ቢወጡና ቢወርዱ ተደብቀው አይቀሩም፡፡
የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና። የማቴዎስ ወንጌል 10፡26
ማንም ሰው በእውነት ላይ ዋሽቶ አይዘልቅም፡፡
ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ። የያዕቆብ መልእክት 3፡14
ሰው ለጊዜው ሊመስለው ይችላል እንጂ ከእውነት ተቃራኒ ሆኖ የሚፀና ሰው ከሰማይ በታች አንድም ሰው የለም፡፡
ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና። 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 13፡8
የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል፤ እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም። ወደ ዕብራውያን 4፡12-13
የጊዜ ጉዳይ ነው የሰዎች የልብ ሃሳብ ይገለጣል፡፡
ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ በእሳት ስለሚገለጥ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3፡12-13
ሰዎች በጊዜው ሁሉንም ወደ ብርሃን የሚያመጣውን እንዳይቀድሙ መፅሃፍ ቅዱስ ያስተምራል፡፡ እግዚአብሄር በጊዜው የሰውን የልብ ምክር ይገልጣል፡፡
ስለዚህም በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል። 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4፡5
እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ክፉም ቢሆን፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና። መጽሐፈ መክብብ 12፡14
አቢይ ዋቁማ ዲንሳ Abiy Wakuma Dinsa
ለተጨማሪ ፅሁፎች https://www.facebook.com/abiy.wakuma/notes
ለቪዲዮ መልእክቶች https://www.youtube.com/user/awordm/videos

#ኢየሱስ #ጌታ #እግዚአብሄርቃል #ህያው #መንፈስ #ነፍስ #ልብ #በጨለማ #በብርሃን #ይገለጣል #የተከደነ #የተሰወረ #የሚሰራ #ቃልኪዳን #የተሳለ #ጤንነት #ለውጥ #ንፁህ #አትለፍ #ትምህርት # #ፍሬ #አማርኛ #ስብከት #መዳን #መፅሃፍቅዱስ #አትጨነቁ  #አቢይ #አቢይዋቁማ #አቢይዋቁማዲንሳ

No comments:

Post a Comment